Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Serayien Yeserahelegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ ፡ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ

ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ ፡ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ

አማኑኤል ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

አማኑኤል ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

ተራራውን ፡ ንዶ ፡ ሜዳ ፡ ካደረገው

መራመድ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ሚጠበቀው

ተራራውን ፡ ንዶ ፡ ሜዳ ፡ ካደረገው

መራመድ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ሚጠበቀው


ጐዳናዬ ፡ ቀንቶ ፡ ተራመድ ፡ ብሎኛል

ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል

ጐዳናዬ ፡ ቀንቶ ፡ ተራመድ ፡ ብሎኛል

ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል

ማን ፡ ይቃወመኛል

ማን ፡ ይቃወመኛል

የቱ ፡ ይይዘኛል

የቱ ፡ ይይዘኛል


አልፈራም ፡ ልቤ ፡ አይሰጋ ፡ ጌታዬ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋ

አልፈራም ፡ ልቤ ፡ አይሰጋ ፡ የጠራኝ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋ

አይቆምም ፡ ምንም ፡ ከፊቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጉልበቴ

እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጉልበቴ (4)

ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ ፡ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ (2)

አማኑኤል ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (2)

ኢየሱሴ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ


ሰባሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊት ፡ ወጥቷልና

ሃሳቤ ፡ ተሳክቶ ፡ መንገዴም ፡ ተቃና

ሰባሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ ከፊት ፡ ወጥቷልና

ሃሳቤ ፡ ተሳክቶ ፡ መንገዴም ፡ ተቃና

የነሃሱን ፡ ደጆች ፡ በስልጣን ፡ ሰበረው

እኔም ፡ ሰባብሬ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አልፌያለው

ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አልፌያለው(4)


አልዝልም ፡ እኔ ፡ አልደክምም ፡ ስራዬ ፡ አያሰለችም

አልዝልም ፡ እኔ ፡ አልደክምም ፡ ስራዬ ፡ አያሰለችም

ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ስላለ ፡ ይሄዳል ፡ እየጨመረ

ይሄዳል ፡ እየጨመረ(4)


ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ ፡ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ....


ታማኝ ፡ ነው ፡ የጠራኝ ፡ ጌታ ፡ ለምንም ፡ ትጥቄ ፡ አይፈታ

ታማኝ ፡ ነው ፡ የጠራኝ ፡ ጌታ ፡ ለምንም ፡ ትጥቄ ፡ አይፈታ

ብርቱ ፡ ነው ፡ በቃሉ ፡ የፀና ፡ ይመራኛል ፡ በድል ፡ ጐዳና

ይመራኛል ፡ በድል ፡ ጐዳና(4)

ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ ፡ መንገዴን ፡ ያቀናህልኝ....

ከፍ ፡ በል ፡ ብል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል

ተባረክ ፡ ብል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል

ተመለክ ፡ ብል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል ይሄ ፡ መች ፡ ይበቃሃል