Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Ezekerewalew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ አያሌው
አልበም ፡ ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ
ርዕስ ፡ እዘክረዋለሁ ፡ ስምህን

አዝ
እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪x)


በስራው ፡ የበረታ ፡ ማዳኑ ፡ ወደር ፡ የለው
ጌታዬ ፡ ወደር ፡ የለው (፪x)
አደርጋለሁ ፡ እንዳለ ፡ እንዲሁ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ነው
እንዲሁ ፡ እንደቃሉ ፡ ነው ፡ እንዲሁ ፡ እንደቃሉ ፡ ነው (፪x)
አስገርሞኛል ፡ ትላቅነቱ ፡ እዘምራለው ፡ ለጌትነቱ (፪x)

አዝ

እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (፪)


ሞትን ፡ የሰባበረ ፡ ሲኦልን ፡ ድል ፡ የነሳው
ሲኦልን ፡ ድል ፡ የነሳው (3x)
ዛሬ ፡ ከመቃብር ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ የሚዘከረው
ስራው ፡ የሚነገረው ፡ ስራው ፡ የሚነገረው (2x)
የትንሳኤ ፡ አምላክ ፡ ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ነህ
በፈጠርካቸው ፡ ትመለካለህ (2x)

አዝ

እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (2x)


የሃያላኖች ፡ ሃያል ፡ ስሙ ፡ ነው ፡ የከበረ
ስሙ ፡ ነው ፡ የከበረ (2x)
ሁሉን ፡ በስልጣኑ ፡ ቃል ፡ አቆመ ፡ እየደገፈ
አቆመ ፡ እየደገፈ ፡ አቆመ ፡ እየደገፈ (2x)
የሰማይ ፡ የምድር ፡ ሁሉ ፡ ፈጠሪ
ዘመኑ ፡ አያልቅ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ (2x)

አዝ
እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
እሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (2x)


አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ሆይ ፡ ዙፋንህ ፡ የፀና
ዙፋንህም ፡ የፀና (2x)
ዘመናት ፡ አይለውጡህ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና
ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገናና (2x)
አይገረሰስ ፡ ፅኑ ፡ መንግሥትህ
እርጅና ፡ አያውቀው ፡ የአንተ ፡ አገዛዝህ (2x)

አዝ
እዘክረዋለው ፡ ስምህን ፡ እናገረዋለው ፡ ስራህን
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ
አልቆጥብም ፡ ድምጼን ፡ ከፍ ፡ አድርጌ
ይሄ ፡ ነው ፡ እላለው ፡ አምላኬ (2x)