Yosef Kassa/Zemetaw/Yihie New Yegebagn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ ካሳ ሌላ ፡ ሥም ፡ ጆሲ ርዕስ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ አልበም ፡ ዝምታው

ውሰድልኝ ፡ ዛሬ ፡ ከነፍሴ ፡ የሆነ ፡ አምልኮዬን

አላገናኘውም ፡ ከሁኔታ ፡ ጋራ ፡ ዝማርዬን

ተላንት ፡ አመስግኜ ፡ ዛሬን ፡ አላማህም ፡ እንዲህ ፡ ብዬ

ይጨምራል ፡ እንጂ ፡ አላሳንሰውም ፡ ምስጋናዬ


የማየው ፡ ነገር ፡ ከምስጋናዬ ፡ አያግደኝም

የምሰማው ፡ አንተን ፡ ከማምለክ ፡ አያስቆመኝም

ምድረበዳዬን ፡ አለምልሞታል ፡ እያየ ፡ አይኔ

በህሩን ፡ ከፍሎ ፡ ያሻግረኛል ፡ አምናለሁ ፡ እኔ


አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር

ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x)



የለመንኩትን ፡ የጠየኩትን ፡ ጥያቄ ፡ ሁሉ

ከምስጋና ፡ ጋር ፡ እጠብቃለሁ ፡ አምኜ ፡ ቃሉን

የከበደኝን ፡ ሸክሜን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ

በአንዳች ፡ ነገር ፡ አልጨነቅም ፡ አለ ፡ ጌታዬ


አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x)


ደመና ፡ የለም ፡ አይታየኝም ፡ በዓይኔ

ነፋሥም ፡ የለም ፡ አይታየኝም ፡ በዓይኔ

ሳላይ ፡ አምናለሁ ፡ እንዲሀ ፡ ይሆናል

ባዶ ፡ ሸልቆ ፡ ውኃ ፡ ይሞላል


አዝ ይሄ ፡ ነው ፡ የገባኝ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ መዘመር ሁኔታው ፡ እያለ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማክበር (፪x)


ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ

አይቻለሁኝ ፡ ሲሰራ

ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ

ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ኃይለኛ

ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ

ድንቅ ፡ ነው ፡ ተአምረኛ

ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ

አይቻለሁኝ ፡ በዓይኔ

ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ