Yosef Kassa/Nuroyie Bekidan New/Kengedihema

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ ካሳ
ርዕስ ፡ ከእንግዲህማ
አልበም ፡ ኑሮዬ ፡ በኪዳን ፡ ነው

ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ነበር
ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ
ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን አንስቼ
የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው (፪x)

ያሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ ያን ፡ የትላንቱን (፫x)
አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያን ፡ ሃይሉን ፡ ሳምን (፫x)
በእውነት ፡ ላመልከው ፡ ከልቤ ፡ ስነሳ (፫x)
ሁሉን ፡ አሳመረው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፫x)

አዝ

ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ
ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ
ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ጋራ
ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም
ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ነውና
ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፪x)

ፊቴ ፡ የቆመውን ፡ ባሕር ፡ ያኔ ፡ አሳልፎኝ ፡ ነበር
ዛሬስ ፡ ደግሞ ፡ ሌላው ፡ ቢገጥመኝ ፡ በየተራ ፡ ቢሰለፍብኝ
ዓይኔን ፡ ማንከራተቱን ፡ ትቼ ፡ ልምታ ፡ ከበሮዬን ፡ አንስቼ
የሰልፉ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ ጠላቴን ፡ ሊያዋርደው

የቆመው ፡ ተራራ ፡ ፊቴ ፡ ተከምሮ (፪x)
አይመስልም ፡ ሚታለፍ ፡ እንደሚከብድ ፡ ሆኖ (፪x)
ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ለአምላኬ ፡ መቼ ፡ አስቸገረው (፪x)
በተአምራቱ ፡ ሁሉን ፡ ሜዳ ፡ አደረገው (፪x)

አዝ

ከእንግዲህማ ፡ ወስኗል ፡ ልቤ
ከእንግዲህማ ፡ ምንም ፡ ላይፈራ
ከእንግዲህማ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ከእንግዲህማ ፡ ሌላውን ፡ አልሰማም
ከእንግዲህማ ፡ ከንቱ ፡ ነውና ፡ ከእንግዲህማ ፡ እዘምራለው ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ፡ ከልቤ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነውና (፬x)