Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Weletaw Bezabegn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ በቀለ ርዕስ ፡ ውለታው ፡ በዛብኝ አልበም ፡ ባለውለታዬ ፡ ጌታ

ዛሬ ፡ ልጅ ፡ ተብዬ ፡ ክብርን ፡ አግኝቻለሁ
የቀድሞ ፡ ኑሮዬን ፡ ረስቼዋለሁ
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፡ ሰው ፡ አድርጐ ፡ አቆመኝ
የመረጥኩህ ፡ ልጄ ፡ እስራኤል ፡ ሆይ ፡ አለኝ
የመረጥኩህ ፡ ልጄ ፡ የምወድህ ፡ ሆይ ፡ አለኝ

አዝ
ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው
ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው
አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ
እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ
ይኸው ፡ ይድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ
ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ (፪x)

በክርስትናዬ ፡ እድሜን ፡ ቆጥሬያለሁ
በልማዳዊ ፡ ሕይወት ፡ ተመላልሻለሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ነፍሴ ፡ አወቀችህ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ውዴ ፡ ነህ ፡ አለችህ
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አባቴ ፡ አለችህ

አዝ
ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው
ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው
አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ
እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ
ይኸው ፡ እድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ
ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ (፪x)

የስጋዬን ፡ ሳስብ ፡ እንዲያው ፡ ስቅበዘበዝ
ጠላት ፡ ቤቴ ፡ ገብቶ ፡ ምርኮን ፡ ሲበዘብዝ
እርሱ ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ አሰበኝ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ
ኃይሌም ፡ ተመለሰ ፡ ጠላቴም ፡ ተረታ
ኃይሌም ፡ ተመለሰ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ

አዝ
ኧረ ፡ ይህን ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልባርከው
ውለታው ፡ በዛብኝ ፡ ከአይምሮዬም ፡ በላይ ፡ ነው
አቤት ፡ ምህረቱ ፡ ምን ፡ እከፍለዋለሁ
እኔም ፡ ክብር ፡ አግኝቼ ፡ አገልጋል ፡ ሆኛለሁ
ይኸው ፡ እድረስልኝ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋናዬ ፡ ኤሄሄ
ማለት ፡ ችያለሁኝ ፡ እኔም ፡ አባብዬ