From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
የደህንነቴ ፡ መደምደሚያ
የክብር ፡ ስሜ ፡ ነህ ፡ መጠሪያ
ማዕረጌ ፡ ሆነህ ፡ በሞትህ
እኔም ፡ ተባልኩኝ ፡ ልጅህ (፪x)
የሞትህ ፡ ፍሬ ፡ የድካምህ
በጣር ፡ የወለድከኝ ፡ ልጅህ
በመከራ ፡ አልፈህ ፡ ያገኘኀኝ
የዕንባህ ፡ ልጅህ ፡ ነኝ (፪x)
አዝ:- እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ
የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ውለታህ ፡ ያለብኝ
እንዴት ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ነው
መክፈል ፡ የምችለው ፡ የፍቅርህን ፡ ሸክም
መቼም ፡ የማልመልሰው
ልክፈል ፡ እንኳን ፡ ብዬ ፡ ብጀምር ፡ ማለዳ
ፍቅርህን ፡ እንዲያው ፡ ሰጥተኀኛል
ታዲያ ፡ አይደለሁም ፡ ወይ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ
መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ
ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ
እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ
አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ
አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ
እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ
ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ
መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ
አዝ:- ንግሥና ፡ መጣ ፡ በደምህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ክነቱም ፡ መጣ ፡ በሞት - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ደህንነት ሆነ ፡ በጸጋ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ልጅ ፡ መባል ፡ ቢሆን ፡ በስራህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
እኔማ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ
የምህረትህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
መራመድ ፡ አልችልም ፡ እግሬ
ተይዣለሁ ፡ እኔ
ነፍሱን ፡ ለወዳጁ ፡ ሚሰዋ
ይገኝ ፡ ይሆናል ፡ በመከራ
ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ ግን ፡ ሚገርመው
ለጠላትህ ፡ የሞትከው (፪x)
እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ የሚገዛ
ልቤን ፡ የያዘ ፡ ውለታህ
የፍቅር ፡ ዕዳ ፡ አኖርክብኝ
ሳልወድህ ፡ ወደድከኝ (፪x)
አዝ:- መልክህና ፡ ውበትህ ፡ ጠፋ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
በሰው ፡ ተንቀህ ፡ ተጠላህ - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ተፈወስኩኝ ፡ አንተ ፡ ቆስለህ - እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
ደዌ ፡ ህመሜን ፡ ወሰድህ - ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
</poem>
|