Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Yenazretu Eyesus

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ

ጊዜው ፡ ትዝ ፡ ይለናል ፡ የተጠራንበት ትዳሩን ፡ ሊያሸንፍ ፡ ሁሉም ፡ በያለበት ሲወጣና ፡ ሲወርድ ፡ አግኝተህ ፡ ስትጠራው አልማረክ ፡ ብሎ "እምቢ" ያለ ፡ ማነው

አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው

ደንቆሮዎች ፡ የነበርን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ሰማን ከብርና ፡ ከወርቅ ፡ መብለጥህን ፡ ተረዳን ሙታን ፡ ስታስነሳ ፡ እውር ፡ ስታበራ ዓይናችን ፡ አይቶሃል ፡ ድንቅ ፡ ሥራ ፡ ስትሰራ

አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው ፡ የሚናወጠውን ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው

ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስንጓዝ ፡ በዓለም ፡ ማዕበል ውስጥ ነፋሱን ፡ ገሰጽከው ፡ እኛ ፡ እንዳንሰምጥ ድምፅህ ፡ አይዘነጋም ፡ ያ ፡ የሚያጽናናው ፍቅርህ ፡ እንደ ፡ ጠል ፡ ነው ፡ ለጠወለገ ሰው

አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው