Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Nefsie Wede Amlakua

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ

አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ

ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው ፡ ሲመጣ ፡ ጌታቸው በመክሊታቸው ፡ የሰሩ ፡ ምሥጋና ፡ አላቸው አገልግሎቱን ፡ ያልናቀ ፡ በጥቂቱ ፡ ታምኖ ብድራቱን ፡ ይቀበላል ፡ ሥራው ፡ ተፈትኖ

አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ

አደራው ፡ ከቶ ፡ የማይገዳቸው ፡ ቸልተኞች የጌታቸውን ፡ መመለስ ፡ የረሱ ፡ ዝንጉዎች ዕድላቸው ፡ ለቅሶ ፡ ነውና ፡ ዋይታ ፡ እንዳይጠብቀኝ መንፈስህ ፡ ዘወትር ፡ ያንቃኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ

አዝ ነፍሴ ፡ ወደ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ

ጥቂት ፡ ታይቶ ፡ ኋላ ፡ እንደሚጠፋ ፡ እንፋሎት እንደ ፡ ሆነ ፡ መች ፡ አጣሁት ፡ ከቶ ፡ የእኔ ፡ ሕይወት እንግዲያው ፡ ታከተኝ ፡ ሳልል ፡ ልሩጥ ፡ ለጌታዬ የሰነፍ ፡ ሰው ፡ ሞት ፡ እንዳልሞት ፡ ልፅና ፡ በዓላማዬ

አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ

መልካሙን ፡ ገድል ፡ ተጋድያለሁ ፡ አበቃሁኝ ኃይማኖትን ፡ ጠብቄያለሁ ፡ ሩጫውን ፡ ጨረስኩኝ እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ ለማለት ፡ ተፈፀመ ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ምሥጋናዬንም ፡ እንዳቀርብ ፡ ለሠራዊት ፡ ንጉሥ

አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ