Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Kamlakachew Beqer
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ከአምላካቸው ፡ በቀር
አዝ ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ማንንም ፡ እንዳያመልኩ ለወርቁ ፡ ምስል ፡ እንዳይሰግዱ ፡ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን ፡ አሳልፈው ፡ የሰጡትን ወዳጆቹን ፡ ያዳነ ፡ በእርሱ ፡ የታመኑትን የሲድራቅ ፡ የሚሳቅ ፡ የአብድናጐም ፡ አምላክ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይባረክ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚያድን ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ የለምና ከእቶኑ ፡ እሳት ፡ ሊያድናቸው ፡ ችሏልና ማዳን ፡ የእርሱ ፡ ነውና (፪x)
አዝ ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ማንንም ፡ እንዳያመልኩ ለወርቁ ፡ ምስል ፡ እንዳይሰግዱ ፡ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን ፡ አሳልፈው ፡ የሰጡትን ወዳጆቹን ፡ ያዳነ ፡ በእርሱ ፡ የታመኑትን የሲድራቅ ፡ የሚሳቅ ፡ የአብድናጐም ፡ አምላክ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይባረክ
ጌታ ፡ ተናገረ ፡ እኔም ፡ ይህንን ፡ ብቻ ፡ ሰማሁ ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ መሆኑን ፡ ተገነዘብሁ እሳቱ ፡ ሲያጠፋ ፡ አየሁ (፪x)
አዝ ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ማንንም ፡ እንዳያመልኩ ለወርቁ ፡ ምስል ፡ እንዳይሰግዱ ፡ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን ፡ አሳልፈው ፡ የሰጡትን ወዳጆቹን ፡ ያዳነ ፡ በእርሱ ፡ የታመኑትን የሲድራቅ ፡ የሚሳቅ ፡ የአብድናጐም ፡ አምላክ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይባረክ
ሰውነታችሁን ፡ ብትሰጡ ፡ ሳትሰስቱ እግዚአብሔር ፡ ይሰራል ፡ አይፋጅም ፡ ከቶ ፡ እሳቱ ሥሙን ፡ አስከብሩ ፡ በርቱ (፪x)
አዝ ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ማንንም ፡ እንዳያመልኩ ለወርቁ ፡ ምስል ፡ እንዳይሰግዱ ፡ እንዳይንበረከኩ ሰወነታቸውን ፡ አሳልፈው ፡ የሰጡትን ወዳጆቹን ፡ ያዳነ ፡ በእርሱ ፡ የታመኑትን የሲድራቅ ፡ የሚሳቅ ፡ የአብድናጐም ፡ አምላክ ለዘለዓለም ፡ ይባረክ (፫)