Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Egziabhier Sireda

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

 በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ፈተና ፡ ቢበዛም
 ጌታን ፡ እየጠራ ፡ ንጹህ ፡ ሰው ፡ አይጠፋም
 እጄን ፡ ያዘኝ ፡ ብሎ ፡ ሲጮህ ይሰማዋል
 ከረግረግ ፡ አውጥቶ ፡ በድል ፡ ይመራዋል

አዝ፦
እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

ችግረኛውን ፡ ሊውጥ ፡ ጠላት ፡ ሲገዳደር
በሚያስፈራራ ፡ ቃል ፡ በትዕቢት ፡ ሲናገር
ደርሶ ፡ የሚታደግ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
በሰው ፡ መታመን ፡ ግን ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው

አዝ፦
እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

ያለውን ፡ ተነጥቆ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ አጥቶ
ከአጠገቡ ፡ የሚቆም ፡ ጌታ ፡ ብቻ ቀርቶ
በእንግድነት ፡ አገር ፡ ተገፍቶ ፡ ለሚያልፈው
ተስፋው ፡ መሰረቱ ፡ አምላኩ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ፦
እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር

የቅዱሳን ፡ ረድኤት ፡ ከሰማይ ፡ ይመጣል
ዘመናትን ፡ ቆጥሮ ፡ ጌታ ፡ ይመለሳል
የልጆቹን ፡ እንባ ፡ ከዓይናቸው ፡ ያብሳል
ክብርና ፡ ምሥጋና ፡ ለሥሙ ፡ ይሆናል

አዝ፦
እግዚአብሔር ፡ ሲረዳ ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ
በደልን ፡ ሲያስወግድ ፡ በቅንነት ፡ ፈርዶ
አላያችሁም ፡ ወይ ፡ ወጥመዱ ፡ ሲሰበር
ምርኮኛው ፡ ተለቆ ፡ ማዳኑን ፡ ሲናገር