Tesfaye Gabisso/Yenazretu Eyesus/Bekurenetehen Lemen Shetkew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search


ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ

አዝ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው የማይጠፋውን ፡ ምረጠው ጌታ ፡ ይሻልሃል ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)

ለማያጠግብህ ፡ እሮጠህ ምናምንቴ ፡ ነገር ፡ ወደህ ረብ ፡ ረድኤት ፡ በማይሆነው በኩረነትህን ፡ ሸጥከው

አዝ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው የማይጠፋውን ፡ ምረጠው ጌታ ፡ ይሻልሃል ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)

ብዙዎች ፡ ወደቁ ፡ ተጠልፈው በገንዘብ ፡ ፍቅር ፡ ተነድፈው ብልጽግና ፡ ያታልላል ይሁዳ ፡ ጌታውን ፡ ሽጧል

አዝ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው የማይጠፋውን ፡ ምረጠው ጌታ ፡ ይሻልሃል ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነህ (፪x)

ሰይፍ ፡ ከዋጠው ፡ የበለጠ የኃጢአት ፡ ዱር ፡ ብዙ ፡ ዋጠ አንተን ፡ የዋጠህ ፡ ምንድን ፡ ነው ነፍስህን ፡ አንቆ ፡ የያዘው

አዝ በኩርነትህን ፡ ለምን ፡ ሸጥከው ኢየሱስን ፡ ለምን ፡ ለወጥከው ክብርና ፡ ገንዘብ ፡ ጠፊ ፡ ነው የማይጠፋውን ፡ ምረጠው ጌታ ፡ ይሻልሃል ለዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የሆነ (፪x)