Tesfaye Gabisso/Egziabhier Menfes New/Lamesgeneh Zariem
ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
ርዕስ ፡ ላመስግንህ ፡ ዛሬም
አልበም ፡ እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
ትንፋሼንና ፡ መንገዴ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ አርገህ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቀህ
ከሚጐዳኝ ፡ ነገር ፡ ዘወትር ፡ ጋረድክ ፡ ሰውረህ
ተመሥገን ፡ ከማለት ፡ ሌላ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ
አዝ
ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ
በሀዘን ፡ ስመታ ፡ ሲከፋኝም ፡ አንዳንድ ፡ ጊዜ
ከብዶ ፡ ሲጫጫነኝ ፡ ሲደራረብብኝ ፡ ትካዜ
የመፅናናት ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ደረሰልኝ
የልቤን ፡ ተካፍሎ ፡ አይዞህ ፡ ሊለኝ ፡ ሊያበረታኝ
አዝ
ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ
ራሴን ፡ አውቀው ፡ አለሁ ፡ እጅግ ፡ አስቀያሚ ፡ ነበርኩ
ምስኪን ፡ አላማ ፡ ቢስ ፡ በኃጥያት ፡ የተቅበዘበዝኩ
ግን ፡ እንዲያው ፡ ወደኸኝ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ፡ በአንተ ፡ ብርታት
በቂ ፡ ቃል ፡ የለኝም ፡ ልገልፅ ፡ የውለታህን ፡ ብዛት
አዝ
ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ
አህዛብ ፡ ባያውቁህም ፡ የእኔ ፡ ነፍስ ፡ ግን ፡ ታውቅሃለች
የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ በእየለት ፡ ትናፍቃለች
ያለ ፡ አባትነትህ ፡ መኖር ፡ ከቶ ፡ አይሆንላትም
መሳይ ፡ አጭበርባሪ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ አይነጥላትም
አዝ
ላመስግንህ ፡ ዛሬም ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ስለማይነገር ፡ ስጦታህ ፡ ስላማይቆጠር ፡ ውለታህ
በእውነት ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
ዘላለም ፡ ይወደስ ፡ ይክበር ፡ ታላቅ ፡ ሥምህ