ልጅነቴ ፡ ያላለቀ (Lejenetie Yalaleqe) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ ልጅነቴ ፡ ያላለቀ ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)

በግብዝነት ፡ ተሯሩጬም ፡ ከእውነትህም ፡ ተሳሰቼ
በስሜት ፡ ተገፋፍቼ ፡ የቃልህን ፡ ሙላት ፡ አጥቼ
እንዳልጠፋ ፡ በጠላት ፡ ተጠቅቼ

አዝ፦ ልጅነቴ ፡ ያላለቀ ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)

ለጋነቴ ፡ እኔን ፡ አጋልጦኝ ፡ መከራውም ፡ አጠውልጐኝ
አውሎ ፡ ነፋስ ፡ አፍገምግሞኝ ፡ የአሸዋው ፡ መሠረት ፡ አዝሞኝ
ክፉኛ ፡ ገፍትሮ ፡ እንዳይጥለኝ

አዝ፦ ልጅነቴ ፡ ያላለቀ ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)

ወተት ፡ ብቻ ፡ መጋቱን ፡ ትቼ ፡ አጥንቱንም ፡ ደግሞ ፡ በልቼ
እንደ ፡ ህጻን ፡ ማሰቤ ፡ ቀርቶ ፡ በጐልማሳነት ፡ ተተክቶ
ላይ ፡ እሻለሁ ፡ ሕይወቴ ፡ ተገንብቶ

አዝ፦ ልጅነቴ ፡ ያላለቀ ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)