Tesfaye Gabisso/Christian Teshagere/Zemenu Fetene

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ዘመኑ ፡ ፈጠነ አልበም ፡ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ

አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ

ሰዓቱ ፡ ሊሞላ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው መለከት ፡ ሊነፋ ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው ነገሩ ፡ ሊያከትም ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው ጌታም ፡ ከተፍ ፡ ሊል ፡ በቅርብ ፡ ነው ፡ ያለው

አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ

ሰማያት ፡ ሲከብዱ ፡ ደመናው ፡ ሲጠቁር ምድራችን ፡ ስታምር ፡ ነገር ፡ ሲቀያየር ምን ፡ አዚም ፡ ኖረብን ፡ እንዳናይ ፡ ጊዜ ፡ አጥሮን ተው ፡ ነቃ ፡ እንበል ፡ እናቁም ፡ አንቅልፍን

አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ

ሰዉ ፡ ሲተራመስ ፡ ሞትን ፡ ለመሳለም ከአምላክ ፡ ተለይቶ ፡ በኃጢያት ፡ ሲታመን ጠቢቡ ፡ እንኳን ፡ ሲስት ፡ በሰይጣን ፡ ሲታለል ተነሱ ፡ አንናገር ፡ ለነፍስ ፡ እንታገል

አዝ ዘመኑ ፡ ፈጠነ ፡ ሮጠ ፡ ገሰገሰ የጌታችን ፡ መምጫ ፡ ጊዜያቱ ፡ ደረሰ ሰዎች ፡ ቶሎ ፡ በሉ ፡ መከሩን ፡ ሰብስቡ የተጣለብንን ፡ አደራ ፡ አስቡ

ለራሱ ፡ ያልሞተ ፡ እራሱን ፡ ያልከዳ ጌታ ፡ የማይገዛው ፡ ለኃጥያት ፡ ያልታገለ በምኑ ፡ ይመስክር ፡ ልቡ ፡ ይንቀጠቀጣል ዋጋም ፡ ክፈል ፡ ሲባል ፡ ትቶ ፡ ይፈረጥጣል