Tesfaye Gabisso/Christian Teshagere/Yeseralegnen Denq

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ
ርዕስ ፡ የሰራልኝን ፡ ድንቅ
አልበም ፡ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ

አዝ
የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪)

በእለት ፡ እርምጃዬ ፡ እግሬን ፡ የሱስ ፡ ቀድሞ
ምህረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ተዓምራቱን ፡ ደግሞ
አሳየኝ ፡ አምላኬ ፡ የከበረ ፡ ነገር
እንደዚህ ፡ ሊመራኝ ፡ ወደ ፡ ፃድቃን ፡ አገር (፪x)

አዝ
የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪)

በቀኝ ፡ በግራዬ ፡ አድፍጦ ፡ አድብቶ
መልካም ፡ መሰል ፡ አጥፊ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ
ጌታ ፡ ግን ፡ ሲያድነኝ ፡ በጦር ፡ ተደራጅቶ
ዲያብሎስ ፡ ሊያጠቃኝ
ነበር ፡ ተሰናድቶ (፪x)

አዝ
የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪)

እርሱ ፡ ቅጥር ፡ ሲቀጥር ፡ በእምላኬ ፡ እየዘለልኩ
ወጥመድ ፡ ሲዘረጋ ፡ እኔም ፡ እያመለጥኩ
በእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ በጌታ ፡ እየታመንኩ
ሩጫ ፡ ቀጥላለሁ ፡ ሁሉን ፡ እያሸነፍኩ (፪x)
አዝ
የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ (፪)

በዘለዓለም ፡ መድህን ፡ ከጥልቁ ፡ ወጥቼ
ከአባት ፡ ከእናት ፡ ዘመድ ፡ የሚበልጥ ፡ አግኝቼ
በአህዛብ ፡ መሃከል ፡ ለርሱ ፡ ዘምራለሁ
የከበረ ፡ ሥሙን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ

የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ልባችሁ (፪×)