Tesfaye Gabisso/Awon Yehonal/Yehayalan Hulu Hayal

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ሰማይን ፡ የሰራ ፡ የምድርም ፡ ፈጣሪ

በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ለዘለዓለም ፡ ኗሪ

ገናናነትህን ፡ ሰማያት ፡ ያውቃሉ

ምድርና ፡ ሞላዋም ፡ ይመሰክራሉ።


የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ

የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ

የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ

ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ።


በነገስህ ፡ ጊዜ ፡ ክብርህን ፡ ስትለብስ

ለተጠቃው ፡ ህዝብህ ፡ ፊትህን ፡ ስትመልስ

ድንቅ ፡ አድራጐትህን ፡ በምድር ፡ ስታደርግ

በጽድቅህ ፡ ስትፈርድ ፡ አመጻን ፡ ስትጠርግ።


የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ

የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ

የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ

ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ።


ቃልህን ፡ ስትሰጥ ፡ በሲና ፡ ተራራ

በልጆችህ ፡ ሰፈር ፡ በበረሃው ፡ ስፍራ

በክብር ፡ እሳትህ ፡ ተራራውን ፡ አጤስከው

በመረጥካቸው ፡ ፊት ፡ ክብርህን ፡ ገለጽከው


የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ

የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ

የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ

ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ።


የተዳፈሩህን ፡ የተነሱብህን

ልክህን ፡ ሳያውቁ ፡ የታጠቁብህን

እየቀጣሃቸው ፡ ተረቶች ፡ ሆነዋል

ተፈርተህ ፡ ተከብረህ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ኖረሃል።


የኃያላን ፡ ሁሉ ፡ ኃያል ፡ ነህ

የነገሥታት ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ

የጌቶችም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ

ባለ ፡ ታላቅ ፡ ግርማ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ። x2