Tesfaye Gabisso/Abietu Mebareken Barken/Abietu Mebareken Barken

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አልበም ፡ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ያቤጽንም ፡ ሰምተሃል ፡ እንደዚህ ፡ ሲለምንህ ነፍሱን ፡ ባርከህለታል ፡ አገሩንም ፡ አስፍተህ

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

በልጅህ ፡ ስቃይና ፡ በጣር ፡ የተወለድን እኛም ፡ ፍሬዎችህ ፡ ነን ፡ አስባስበህ ፡ ጠብቀን

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህየእኛ ፡ ተስፋ

ከፊትህ ፡ አትጣለን ፡ እንማጸንሃለን በሞገስህ ፡ አስበን ፡ በምህረትህ ፡ ጐብኘን

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ሰማያቱም ፡ ይከፈቱ ፡ መንፈስህ ፡ ይፍሰስልን ሕይወታችን ፡ ትረስርስ ፡ ነፍሳችን ፡ ትጥገብልን

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

ብቻችንን ፡ አንቅር ፡ አብዛን ፡ እየባረክህ አበልጽገን ፡ በፀጋህ ፡ ታደገን ፡ በቃልህ

አዝ አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን አገራችንን ፡ አስፋ እጅህም ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ ትሁን አንተ ፡ ነህ ፡ የእኛ ፡ ተስፋ

እግዚአብሔርን ፡ በማወቅ ፡ ምድር ፡ እስክትሞላ ምልጃችን ፡ ይቀጥላል ፡ ጉልበታችን ፡ ሳይላላ