Tesfaye Chala/Yebelay Neh Gieta/Aderegelegn Teamer
ርዕስ ፡ አደረገልኝ ፡ ተዓምር ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ አልበም ፡ የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ
እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ መከራዬን ፡ አስረሳኝ
በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ እራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይበዛል ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ባከብረው
ማንም ፡ የማይመስለው ፡ ወዳጅ ፡ አግኝቻለሁ (፬x)
አሃሃ ፡ የጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ አሃሃ ፡ አይ ፡ ማስፈራራቱ
አሃሃ ፡ ከንቱ ፡ ሆኖ ፡ ቀረ ፡ አሃሃ ፡ ቀደመች ፡ ምህረቱ
አሃሃ ፡ ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ አሃሃ ፡ በደመና ፡ መራኝ
አሃሃ ፡ እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ አምላኬ ፡ ከረዳኝ
እረ ፡ ማነው ፡ ከልካይ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ከረዳኝ
አዝ
አደረገልኝ ፡ ተአምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ ሃሃ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
ዘይት ፡ ከማሰሮ ፡ ከማድጋው ፡ አልቆ
ተስፋዬ ፡ ተሰብሮ ፡ ተሰባብሮ ፡ ደቆ
ስሙን ፡ ተጣርቼ ፡ የልቤን ፡ ስነግረው
እፌን ፡ ሞልቶ ፡ በሳቅ ፡ ሕይወቴን ፡ አዳነው
የአምናው ፡ ችግር ፡ ሄደ ፡ ማድጋው ፡ ሙሉ ፡ ነው
ከራሴ ፡ ተርፌ ፡ አለኝ ፡ የምሰጠው
የታምራት ፡ አምላክ ፡ ተአምር ፡ አድርጐልኛል
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይስማው ፡ ነገር ፡ ተገልብጧል
አዝ
አደረገልኝ ፡ ተአምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ ፡ አሃሃ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)
አሃሃ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ ላምጣ ፡ አሃሃ ፡ ላክብረው ፡ ሳልቆጥብ
አሃሃ ፡ እግሮቼም ፡ ይዝለሉ ፡ በፊቱ ፡ ላሸብሽብ
አሃሃ ፡ ክብሬን ፡ ብጥልለት ፡ አሃሃ ፡ የሚንቀኝ ፡ ማነው
አሃሃ ፡ ያደረገልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
አሃሃ ፡ የተሰራልኝን ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው
ሰማይ ፡ ጥርት ፡ አለ ፡ ደመናውም ፡ ጠፋ
የችግሩ ፡ ብርታት ፡ ፊቴን ፡ ለቆ ፡ ጠፋ
የነበረው ፡ ሄደ ፡ ያለውም ፡ አለቀ
ውኃ ፡ ሳይኖርበት ፡ ሸለቆው ፡ ደረቀ
ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ንፋስም ፡ ሳይነፍስ
ዝናባትን ፡ አዞ ፡ ምድርን ፡ ሲያረሰርስ
የጠላቴን ፡ እቅድ ፡ እያፈረሰልኝ
ድል ፡ በድል ፡ ላይ ፡ ለመድኩ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
አዝ
አደረገልኝ ፡ ተዐምር ፡ አደረገልኝ (፪x)
ተራራዬን ፡ ናደው ፡ ናደው ፡ ኦሆሆ ፡ ሸለቆዬን ፡ ሞላ
ባሕሩን ፡ ከፈለው ፡ ኦሆሆ ፡ መንገዴን ፡ አቀና (፪x)