Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Tamagneneteh Bezu Mehereteh Lenie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ ታማኝነትህ ፡ ብዙ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን

ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

በመከራ ፡ ቀን ፡ ስምህን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ ከቶ ፡ አፍሮ ፡ ያውቃል ዓይንህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ በሰማይ ፡ ምስኪኑን ፡ ይመለከታል ታማኝነትህ ፡ የበዛ ፡ ምህረትህ ፡ ወደር ፡ የሌለው አንተን ፡ ተስፋ ፡ ላደረጉ ፡ እርግማኑ ፡ በረከት ፡ ነው

አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ታላቅ ፡ ተራራ ፡ በስምህ ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ይሆናል ማዕበል ፡ ቃልህን ፡ ሰምቶ ፡ ፈጥኖ ፡ ያተዘዝልሃል ህዝብህን ፡ በምድረበዳ ፡ መናን ፡ መመገብ ፡ ታውቃለህ ቃልህን ፡ ለሚጠብቁ ፡ መች ፡ አንተ ፡ ታሳፍራለህ

አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ደካማው ፡ ጉልበቱ ፡ በአንተ ፡ ኃይሉ ፡ እንደንስር ፡ ታደሰ ሃያሉ ፡ ሞገስህን ፡ ሲያይ ፡ ወኔው ፡ ሃሞቱ ፡ ፈሰሰ ብላቴናው ፡ ግን ፡ በሥምህ ፡ ወንጭፍ ፡ ጠጠሩን ፡ ሰንዝሮ አየሁ ፡ ጠላቱ ፡ በቅጽበት ፡ በአደባባይ ተዘርሮ

አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)

ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ስትራ ፡ ማን ፡ ቀርቦ ፡ አንተን ፡ አማክሯል ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ መሆንህን ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይመሰክራል ብቻህን ፡ ለዘለዓለም ፡ ጸንተህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ ነህ አንተን ፡ ታምኜ ፡ እስከዛሬ ፡ ማድጋዬ ፡ መች ፡ ጐደለ

አዝ ታማኝነትህ ፡ ብዙ ፡ ምህረትህ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጐ ፡ ያፈረ ፡ ሰው ፡ ማን ፡ ነው ሁሉንም ፡ በስዓቱ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ ትሰራለህ አማካሪ ፡ አትፈልግም ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኢየሱስ) ነህ (፪×)