Tesfaye Chala/Lebarkew Gietayien Lebarkew/Mesgana Ahahatitle

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

Artist Tesfaye Chala ርዕስምሥጋና ፡ አሃሃ አልበም ፡ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው


ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱሱ ፡ አቻ ፡ አይገኝለት

እንደሞተ ፡ አልቀረም ፡ ከቶ ፡ አለ ፡ በሰማያት

ማን ፡ ይቃወመናል ፡ ዛሬስ ፡ በደሙ ፡ ዋጅቶናል

ትንሴኤውን ፡ ልናወራ (በገና ፡ አንስተናል) (፪x)

(ምሥጋና) (፫x) ለሆነው ፡ ገናና

(ዕልልታ) (፫x) ድል ፡ ላረገው ፡ ጌታ


ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ከዙፋኑ ፡ ወርዶ

የዕዳውን ፡ ጽህፈት ፡ በደሙ ፡ አስወግዶ

ምስኪን ፡ መስሎ ፡ መቶ ፡ ዲያብሎስን ፡ ቀጣ

በጨለማ ፡ ላሉ ፡ አዲስ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ


አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ እየሱስ...


ጐስቋላና ፡ ድሃ ፡ ምስኪን ፡ የህማም ፡ ሰው

ባየነውም ፡ ጊዜ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የሌለው

ፍቅር ፡ ኃይሉ ፡ ሆነች ፡ ድካሙ ፡ በረታ

ማንም ፡ ሳያግዘው ፡ ዲያብሎስን ፡ መታ


አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ...


የጣር ፡ የሰቆቃው ፡ ጩኸቱ ፡ ሲሰማ

መከራው ፡ በዝቶበት ፡ ቢመስልም ፡ ደካማ

ምድር ፡ አልቻለችም ፡ ሞትን ፡ ፈነቀለ

ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ አዲስ ፡ ዘር ፡ በቀለ


አዝ ገናና ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ...


ስሙም ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ የሰላም ፡ አለቃ

ሞትና ፡ ርግማንም ፡ ስቃዩ ፡ አበቃ

ገናና ፡ ገናና ፡ ገናና ፡ ነው ፡ አሱ

በሆታ ፡ በልልታ ፡ ስሙን ፡ አሞግሱ


አዝ ገናና ፡ የስኛ ፡ ኢየሱስ...