Tesfaye Chala/Bamare Qenie/Yehayalan Hayal Yegna Gieta

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search


ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጫላ ርዕስ ፡ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ አልበም ፡ ባማረ ፡ ቅኔ አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

ብዙ ፡ ሃያላኖች ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ነበሩ እንድ ፡ ዘመን ፡ ታይተው ፡ ጠፍተው ፡ በዚያው ፡ ቀሩ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሎ ከበረ ፡ በሰማይ ፡ አሜን ፡ በሞት ፡ ላይ ፡ አይሎ

አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም

የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ማነው ፡ የሚመስለው ፡ የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስ ማህተቡን ፡ ሊፈታ ፡ የቻለው ፡ እርሱ ፡ ነው ይክበር ፡ ዛሬም ፡ አሜን ፡ አዎ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

ማንም ፡ ያልቻለውን ፡ መጋረጃ ፡ ቀዶ ወንጌልን ፡ ሰበከ ፡ ወደ ፡ ሲኦል ፡ ወርዶ ለታሰሩት ፡ ሰላም ፡ መፈታት ፡ አወጀ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ በደሙ ፡ እኛን ፡ ዋጀ

አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም

የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ ኃያል ፡ ንጉሥ እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ክበር ፡ ንገሥ ፡ ለዘላለም

አጋንንት ፡ በሥሙ ፡ ይታዘዙለታል ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ ይላል ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ ባሕሩን ፡ ይከፍላል ጌት ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ አዎ ፡ ዘለዓለም ፡ ይገዛል

አዝ የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የእኛ ፡ ጌታ በሰልፍ ፡ በወጀቡ ፡ የበረታ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)

እንደ ፡ እርሱ ፡ የሆነ ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም እንደ ፡ አንተ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም ይክበር ፡ ይንገሥ ፡ ለዘላለም (፪x)