Teodros Tadesse/Yemot Awaj
Jump to navigation
Jump to search
የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሠራም ፡ በሕይወቴ
አይሆንም በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ ነገሩን/እየሱስ ፡ አባቴ (፪x)
የሚውጠውን ፡ ፈልጎ ፡ እንደሚያገሣ ፡ አምበሳ
ዙሪያ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢያንዣብብ ፡ ሰላሜን ፡ ደርሶ ፡ ሊነሳ
መጣ ፡ ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ ነደደ ፡ የአምላኬ ፡ ቁጣ
በሳት ፡ ቅጥሩ ፡ ቀጠረኝ ፡ ጠላት ፡ በበቀል ፡ ሳይወጣ
ስልጣን ፡ የለውም ፡ በኔ ፡ ላይ
አለቃ ፡ አይሆንም ፡ የበላይ
እንዲያው ፡ አይደለም ፡ መጓደዴ
በመስቀል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ መወለዴ (፬x)
የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሠራም ፡ በሕይወቴ
አይሆንም በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ ነገሩን/እየሱስ ፡ አባቴ (፪x)
የስንቱን ፡ ጀግና ፡ ቤት ፡ ደፍሮ ፡ መቅሰፍቱን ፡ ይዞ ፡ ሲገባ
አሳየኝ ፡ ገና ፡ ከሩቁ ፡ አጥፊውን ፡ ገዳዩን ፡ ሌባ
ሸንጎ ፡ ሰብስቦ ፡ ሲመክር ፡ ታሪኬን ፡ መና ፡ ሊያደርገው
ምልክት ፡ ሰጦ ፡ አስመለጠኝ ፡ እኔ ፡ ማመልከው ፡ እንዲህ ፡ ነው
ስልጣን ፡ የለውም ፡ በኔ ፡ ላይ
አለቃ ፡ አይሆንም ፡ የበላይ
እንዲያው ፡ አይደለም ፡ መጓደዴ
በመስቀል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ መወለዴ (፬x)
የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሠራም ፡ በሕይወቴ
አይሆንም በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ ነገሩን/ኢየሱስ ፡ አባቴ (፪x)
Watch on YouTube