Teodros Tadesse/Wa/Amrolegnal Qenie
< Teodros Tadesse | Wa
ማቄን ፡ ቀደህ ፡ እንባዬን ፡ አበስከው ፡ ቤቴን ፡ አየህው ደረስክልኝ ፡ ለምስጋና ፡ በቃሁ ፡ እኔም ፡ እንደሰው. በቃ ፡ አለፈ ፡ መከራው ፡ ተረሳ ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ አበሳ እንደ ፡ ማርያም ፡ ከበሮን ፡ ሊያነሣ ፡ ልቤ ፡ ተነሳ
ላመሥግንህ ፡ አምሮልኛል ፡ ቀኔ ላዚምልህ ፡ ልቀኝ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ (2x)
ከእናቴ ፡ ማሕፀንማን ፡ ምሳያውቀኝ ፡ የመረጥከኝ.
እንደናት ፡ እንዳባት ፡ በፍቅር ፡ ይዘሕ ፡ ያሳደከኝ
ሰለቸኝ ፡ ታከተኝ ፡ ላፍታ ፡ ሳትለኝ ፡ ከቶ ፡ እስከዛሬ
በኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ ባንተ ፡ አይደለሞይ
በሕይወት ፡ መኖሬ
ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነሕ ፡ ነገም ፡ ተሰፋዬ
የመጨረሻ ፡ መደምደሚያዬ
ላንተ ፡ ዘመኔን ፡ ብሰጥህ ላንተ ፡ ክብር ፡ ነው ፡ ለኔ ይህም ፡ ሲያንስሕ ፡ ነው ፡ አንዲህ ፡ መሆኔ ላንተ ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፡ ገና ፡ ሆናለሁ ምላሽ ፡ ባይሆንም ፡ እዘምራለሁ
እኔ ፡ ማውቀው ፡ መልካምነትህን
ምናገረው ፡ ደግ ፡ መሆንሕን
ሳሞካሸው ፡ ብውል ፡ ደጋግሜ
ሡስ ፡ ሆኖብኝ ፡ ነው ፡ ገብቶ ፡ በደሜ
ያየ ፡ ያውቀዋል ፡ የቀመሠ
በፍቅርህ ፡ ዝናብ ፡ የረሰረሰ
ሰው ፡ እንደሚያይ ፡ አንተ ፡ አታይም
እና ፡ ልቤን ፡ አየኸው
የስውር ፡ ጸሎቴን ፡ ዘልቀሕ ፡ ጓዳዬን
ገብተሕ ፡ ሰማኸው
የማንም ፡ ባለዕዳ ፡ ኸረ ፡ አይደለሕም
ልናገር ፡ እኔ
ስራዬን ፡ ስትሠራው ፡ ሥታሳምረው ፡ ስላየሁ ፡ ባይኔ
የቅርብ ፡ የምልህ ፡ ሚስጥረኛዬ የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ ሑለንተናዬ