Tekeste Getnet/Mekniyatie Bezu New/Mekniyatie Bezu New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተከስተ ፡ ጌትነት ርዕስ ፡ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው Volume 2

አንደበቴ ፡ ከምስጋና ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አያውቅም

ይዘምራል ፡ ላንተ ፡ ክብር ፡ ሰለቸኝ ፡ አይልም

ደግነትህ ፡ በሕይወቴ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ ፡ አሳጣኸኝ ፡ ከቶ ፡ ምለው ፡ ከምሥጋና ፡ ሌላ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ

አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን

ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x)


ከቶ ፡ አልሻም ፡ በዘመኔ ፡ ካንተ ፡ ሌላ ፡ ለኔ

ቆርጫለሁ ፡ ላልለይህ ፡ ኢየሱስ መድህኔ

ብቻ ፡ አንተ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ይሁን ፡ ደስ ፡ እንዳለህ

አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታዬ ፡ ባከብርህ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ

አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን

ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x)


ልማድህ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ማድረግ ፡ ከብረህ ፡ የምታከብር

ትቢያ ፡ አራግፈህ ፡ መሸላለም ፡ ማብቃት ፡ ለቁም ፡ ነገር

ስንቱ ፡ አረፈ ፡ እፎይ ፡ አለ ፡ ወዳንተ ፡ ሲጠጋ

አመለጠ ፡ ባንተ ፡ ጉልበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ (፪x)


አዝ

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ

አጥንቶቼም ፡ በርቱ ፡ ለአምላኬ ፡ ተገዙ

ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አክብሪው ፡ ከሞት ፡ ያዳነሽን

ዝም ፡ አትበይ ፡ ተነሽ ፡ አመስግኝ ፡ ጌታሽን (፪x)


በምስጋና ፡ ላይ ፡ ምስጋና ፡ ገና ፡ አበዛለሁ

ተባረክ ፡ ብዬ ፡ ሁልጊዜ ፡ መቼ ፡ እጠግባለሁ (፪x)


በዝማሬ ፡ ላይ ፡ ዝማሬ ፡ ገና ፡ አበዛለሁ

ተባረክ ፡ ብዬ ፡ ሁልጊዜ Bold textመቼ ፡ እጠግባለሁ (፪x) Bold text