Tekeste Getnet/Mejemeriya/Wetrom

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ተከስተ ፡ ጌትነት
ርዕስ ፡ ወትሮም
አልበም ፡ መጀመሪያ

እኔ ፡ እንደው ፡ ልማዴ ፡ ነው ፡ ሳይነጋ ፡ መዘመር
እኔ ፡ እንደው ፡ ልማድ ፡ አለኝ ፡ ችግር ፡ ፊት ፡ መዘመር
ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኝ ፡ ጀመር
ሁሉ ፡ ደህና ፡ ነው ፡ ስል ፡ ደህና ፡ ሆኖ ፡ ቀረ
አስፈሪው ፡ ተራራ ፡ ሆነ ፡ እንዳልነበረ

ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ

ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ

ልበልህ ፡ ጌታዬ /3×/
ልበልህ ፡ ንጉሴ /3×/

ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ

ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ

የዕለቱን ፡ መስዋዕት ፡ ከእኔ ፡ የሚሻው
ላሳርግለት ፡ ያውድ ፡ መዓዛው
አያፍርም ፡ ፊቴ ፡ እርሱ ፡ ጋ ፡ ደርሶ
ይለውጠዋል ፡ ሁሉን ፡ አድሶ

ጥያቄ ፡ ኖሮ ፡ ያልተመለሰ
መዘመር ፡ አልተው ፡ ፍቅሬም ፡ አልቀነሰ
ማጠኛውን ፡ ስጡኝ ፡ የተራዬን ፡ ልበል
እኔ ፡ ጋር ፡ ደርሶ ፡ አምልኮ ፡ አይጓደል

ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ

ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ

ላስተዋለውማ ፡ ተፈጥሮም ፡ ያወራል
ሊነጋጋ ፡ ሲቀርብ ፡ እጅግ ፡ ይጨልማል
ምልክት ፡ ነበር ፡ ድቅድቅ ፡ ማለቱ
የመጎብኛዬ ፡ ደረሰ ፡ ሰዓቱ

ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ

ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ

ልበልህ ፡ ጌታዬ /3×/
ልበልህ ፡ ንጉሴ /3×/

ድሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ መተህማ ፡ አላሳንስህ

ወትሮም ፡ የበላይ ፡ ነህ
ክብር ፡ ነው ፡ መገኛህ
እኔ ፡ ቤት ፡ ሲሆን ፡ ሲሆን ፡ አልቆጥብብህ