Tekeste Getnet/Mejemeriya/Alteganenem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አልተጋነነም ፡ የእስካሁኑ

የተነገረው ፡ በየቀኑ

አትጨረስም ፡ ተብራርተህ

ከተባለልህ ፡ በላይ ፡ ነህ


ትልቅ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቅ

ማንንም ፡ ደግሞ ፡ የማይንቅ

አለ ፡ በማደሪያው/ በሰማያት ፡ አለ

ቸርነቱ ፡ ያልተጓደለ


አማኝ ፡ አልሻም ፡ ማጋነኛ

ታላቅነትህን ፡ ለማስረጃ

አይቸዋለው ፡ በህይወቴ

ማእረጌ ፡ ሆነህ ፡ ገብተህ ፡ እቤቴ


የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል

ስራህ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ከአይምሮ ፡ ያልፋል

የጠቢብ ፡ ጥበብ ፡ ያዋቂው

አንተን ፡ አይገልጥህ ፡ ተራኪው


ትልቅ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቅ

ማንንም ፡ ደግሞ ፡ የማይንቅ

አለ ፡ በማደሪያው/ በሰማያት ፡ አለ

ቸርነቱ ፡ ያልተጓደለ


ከሚገርመኝ ፡ ከሚደንቀኝ ፡ ነገር ፡ አንዱ

እግዚአብሄር ፡ እኔን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ እኔን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ ትንሹን ፡ መውደዱ


ከሚገርመኝ ፡ ከሚደንቀኝ ፡ ነገር ፡ አንዱ

እግዚአብሔር ፡ ደሃውን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ እኔን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ መውደዱ

እግዚአብሔር ፡ እኔን ፡ መውደዱ