Tamrat Haile/Ahunem Alehu Bemerkebu/Sedom Gemora

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አዝ

ሰዶም ፡ ገሞራ (፬x)

ሰው ፡ እግዚአብሔርን ፡ አይፈራ ሰዶም ፡ ገሞራ

ግርግር ፡ ነው ፡ ከተማው አንዱ ፡ ሌላውን ፡ አይሰማው ሁሉም ፡ ይሮጣል ፡ ለንግዱ ጐዳናው ፡ ጠቧል ፡ መንገዱ ለነፍሱ ፡ አያስብ ፡ ለሰማይ ፡ ቤቱ ለዛሬ ፡ ብቻ ፡ ለለት ፡ ለለቱ

አዝ ሰዶም ፡ ገሞራ (፬x) ሰው ፡ እግዚአብሔርን ፡ አይፈራ ሰዶም ፡ ገሞራ

ወንድ ፡ ከወንድ ፡ ጋብቻ ሴትም ፡ ከሴት ፡ ጋር ፡ ጋብቻ በፍትወት ፡ እሳት ፡ ሲቃጠል ሲጋደም ፡ በየስርቻ እንሰሳ ፡ ሆነ ፡ ይሄ ፡ ክቡር ፡ ሰው መድኋኒት ፡ የለሽ ፡ ደዌ ፡ ጨረሰውድ

አዝ ሰዶም ፡ ገሞራ (፬x) ሰው ፡ እግዚአብሔርን ፡ አይፈራ ሰዶም ፡ ገሞራ

ሕጻን ፡ አይሉ ፡ አዋቂ አንዱ ፡ በሌላው ፡ ሸማቂ ቀድሞ ፡ ጣዩ ፡ አልታወቀ ፡ እንጂ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ጨብጧል ፡ ፈንጂ የፍቅር ፡ ኑሮ ፡ የዕርቅ ፡ ሰላም ክፋት ፡ ጠረገው ፡ ጠፋ ፡ ካለም

አዝ ሰዶም ፡ ገሞራ (፬x) ሰው ፡ እግዚአብሔርን ፡ አይፈራ ሰዶም ፡ ገሞራ

ልጅ ፡ የናቱን ፡ ሆድ ፡ ረገጠ አባትም ፡ ልጁን ፡ ገላመጠ እናትም ፡ ጣለች ፡ ልጇን ቀረቀረችው ፡ ደጇን ጣራው ፡ ዘበጠ ፡ ቤቱ ፡ ተናጋ ዳኛ ፡ ጠፋና ፡ የሚያረጋጋ

አዝ ሰዶም ፡ ገሞራ (፬x) ሰው ፡ እግዚአብሔርን ፡ አይፈራ ሰዶም ፡ ገሞራ