Tamrat Haile/Ahunem Alehu Bemerkebu/Ahunem Alehu Bemerkebu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ታምራት ፡ ሃይሌ
ርዕስ ፡ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
አልበም ፡ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ

አዝ

አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ተሳፍሬአለሁ ፡ በባቡሩ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከሰፈሩ
መቆም ፡ አልሻም ፡ በመንገዱ
ይቆራርጣል ፡ ሐዲዱ

አዝ

አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ


ስንቶች ፡ ተጓዙ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ሸለቆ ፡ ወርደው ፡ ወጡ ፡ ተራራ
እየመሰለኝ ፡ ከጐኔ ፡ እያሉ
እኔ ፡ መች ፡ አወቅሁ ፡ እንደተበሉ


አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ


ሳይመርምሩ ፡ ጊዜ ፡ ዘመኑን
ሳያውቁት ፡ ውኋው ፡ ጥልቅ ፡ መሆኑን
መንሸራሸር ፡ እያማራቸው
ሳያውቁት ፡ ድንገት ፡ ውጦ ፡ አስቀራቸው


አዝ አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

ስንቱን ፡ አልፌ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ
በፀጋው ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ በራሴ
ጌታ ፡ ሰጥቶኛል ፡ አቅሜን ፡ መለኪያ
ከፀጋው ፡ በቀር ፡ የለኝ ፡ መመኪያ



አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ

መርከቡ ፡ ሲቆም ፡ በየወደቡ

ወራጁን ፡ ሲያወርድ ፡ ሌሎች ፡ ሲገቡ በየከተማው ፡ ባቡሩም ፡ ሲያልፍ እንዱን ፡ ሲያሳፍር ፡ ሌላውን ፡ ሲያራግፍ ከጫፍ ፡ የሚደርስ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ እንጃ አጽናኝ ፡ እያልኩኝ ፡ ይዣለሁ ፡ ምልጃ
አሁንም ፡ አለሁ ፡ በመርከቡ
ገና ፡ አልደረሰም ፡ ከወደቡ
መውረድ ፡ አልሻም ፡ እጓዛለሁ
ውኋ ፡ እንዳይበላኝ ፡ እፈራለሁ