ሙሉቀን መለሰ (Muluken Melese)
Jump to navigation
Jump to search
ስለምሕረትህ ፡ ስለጥበቃህ
ስለውለታህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ
ከበርት ፡ ወይፈኑን ፡ ከአዝርትም ፡ ምርጡን
ከሐብት ፡ ከበረክት ፡ ከአስራት ፡ ምጽዋቱን
ነፍሰእንም ፡ ጨምረእ ፡ ሚዛን ፡ ላይ ፡ ብሰፍረው
ጌታ ፡ ለውለታህ ፡ እጅግ ፡ ያነሰ ፡ ነው
በተለምዶ ፡ ቃላት ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ሌላማ ፡ ምን ፡ አለኝ ፡ ላንተ ፡ የምሰጥህ
አምላክ ፡ ሆይ ፡ ውለታህ ፡ እጅግ ፡ የበዛ ፡ ነው
ቤት ፡ አልሰራልህም ፡ ዙፋንህ ፡ ሰማይ ፡ ነው
ብር ፡ ወርቁ ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ
ብቻ ፡ በአንደበቴ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ
እንደዳዊት ፡ ልዝለል ፡ ልዘምር ፡ ልጨፍር
አዳኝነትህን ፡ ገድልህን ፡ ልናገር
ጌታ ፡ ለውለታህ ፡ የለም ፡ የምከፍልህ
የኔ ፡ ታሪክ ፡ ድርሻ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ ፡ ነው
ሐጥያት ፡ መስራት ፡ ትቼ ፡ ወዳንተ ፡ ብመለስ
በአለም ፡ ዙሪያ ፡ ሮጬ ፡ ወንጌልን ፡ ባዳርስ
ሰማይና ፡ ምድርን ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ ባስስ
ጌታ ፡ ውለታህን ፡ አልችልም ፡ ልመልስ