ያ መሲሕ (Ya Messih) - መስከረም ፡ ጌቱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem Getu)

፫
(3)

Ya Messih
(Ya Messih)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2024)
ቁጥር (Track):

፬ (4)

ርዝመት (Len.): 5:46
ጸሐፊ (Writer): መስከረም ፡ ጌቱ
(Meskerem GetuProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስከረም ፡ ጌቱ ፡ አልበሞች
(Albums by Meskerem Getu)

ዝቅ ብሎ መጣ አነሰ ስለኛ
ክፋት እንዳረገ ወንበዴ ፍርደኛ
የሰው ልጅ እርቃኑን በመስቀል ላይ ታየ
በዚያ በጎልጎታ በቀራንዮ ቆየ

እ ያ መሲሕ ዝቅ አለ
እህ ያ ንጉስ ዝቅ አለ
እ ከአብረሃም በፊት የነበረው እርሱ ሰው ሆነ
እህ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ

እ ተዋረደ ሆነ የተጠላ
እህ ተገረፈ መከራውን በላ
እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆነ
እህ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ

እንዲያ ሲያናንቁት አንዳች አልመለሰ
ሲዘባብቱበት ሲሰድቡት ታገሰ
እጁ ባበጃጀው እጅ ላይ ወደቀ
የህመም ሰው ሆነ በደዌ ደቀቀ

እ ያ መሲሕ ዝቅ አለ
እህ ያ ንጉስ ዝቅ አለ
እ ከአብረሃም በፊት የነበረው እርሱ ሰው ሆነ
እህ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ

እ ተዋረደ ሆነ የተጠላ
እህ ተገረፈ መከራውን በላ
እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆነ
እህ የአለም ፈጣሪ ሰው ሆነ

ተንኮል የሌለበት ፃድቅ ሆኖ ሳለ
ደዌአችንን ወስዶ ስለኛ ቆሰለ
የሁላችን በደል በእርሱ ላይ ሆነ
ነፍሱን አሳልፎ ለሞት አቀረበ

የድል ንጉስ/4
እንደሞተ አልቀረም ተነስቷል እየሱስ
የድል ንጉስ/4
እንደሞተ አልቀረም ተነስቷል እየሱስ

መቃብሩ ባዶ ነው
የኛ ጌታ ህያው ነው
መቃብሩ ባዶ ነው
በዚያ የለም ህያው ነው

ህያው ነው/4