Mesfin Mamo/Shilimateh Neh

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

'አንተ ፡ ግን' ሁኔታውን ፡ ስናይ ፡ እየሆነ ፡ ያለውን ከቁጥጥር ፡ ውጪየሆነ ፡ የሚመስለውን ለምን ፡ ይኼ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለ ስትል ፡ ነፍስ ፡ ስትቃትት ፡ አረ ፡ ያምላክ ፡ ያለህ አንተ ፡ ግን ፡ በዙፋንህ ፡ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም ፡ አውቀህ እግዚአብሔር ፡ ከጅማሬ ፡ እስከ ፡ ፍፃሜው ባለቤት ፡ ነህ ፡ የታሪክ ፡ ፀሐፊው ባንተ ፡ ማረፍ ፡ ነው ፡ መልካሙ ፡ ምርጫ ሌላ ፡ እኮ ፡ የለም ፡ ከተ ፡ ያለው ፡ ብልጫ ኑሮ ፡ ሲወሳሰብ ፡ ሰው ፡ ግራ ፡ ገብቶት ነገ ፡ አልታይ ፡ ብሎት ፡ ውሉ ፡ ሲጠፋበት እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን ፡ ይኼ ፡ ሆነ እያለ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንቅልፍ ፡ ከዓይኑ ፡ ሸሸ አንተ ፡ ግን ፡ በዙፋንህ ፡ ተረጋግተህ ተቀምጠሃል ሁሉንም ፡ አውቀህ እግዚአብሔር ፡ ከጅማሬ ፡ እስከ ፡ ፍፃሜው ባለቤት ፡ ነህ ፡ የታሪክ ፡ ፀሐፊው ባንተ ፡ ማረፍ ፡ ነው ፡ መልካሙ ፡ ምርጫ ሌላ ፡ እኮ ፡ የለም ፡ ከቶ ፡ ያለው ፡ ብልጫ ሁሉ ፡ እኮ ፡ በእጅህ ፡ ነው ሃሳብህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ላመኑብህ ፡ መታመኛ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ መዳኛ