Mesfin Gutu/Teshager Yalew/Ante Yenie
ርዕስ አንተ የኔ ዘማሪ ፡ መስፍን ፡ ጉቱ Volume 3 አልበም ፡ ተሻገር ፡ ያለው
አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ
ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ
በጨለማዬ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፡ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x)
ማን ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ማን ፡ ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x)
ማን ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ማን ፡ ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x)
ተማመለህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
በጭንቅ ፡ የወለድከኝ ፡ በጎልጎታ
እድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ሰጥሃለሁ
ዘላለም ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ፡ እገዛለሁ
ታዲያ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ልቀኝ ፡ እንጂ
ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ
ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x)
እንደመሸ ፡ አይቀርም ፡ ለሊቱ ፡ ይነጋል (፬x)
ማንጋት ፡ ልማድህ ፡ ነውና
ማንሳት ፡ ልማድህ ፡ ነወና
ማክበር ፡ ልማድህ ፡ ነወና
ማስዋብ ፡ ልማድህ ፡ ነውና
ውዴ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ደግሞ ፡ የእርሱ ፡ ነኝ ፡ የየሱስ ፡ ነኝ (፪x)
ማንም ፡ አይገባም ፡ በመሀላችን
ጉድለት ፡ የሌለበት ፡ ነው ፡ ፍቅራችን
ጊዜም ፡ ሁኔታም ፡ አይሽረዉም ፡ ለኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ልዩ ፡ ነዉ ፡ ልዩ ፡ ነዉ (፪x)
ታዲያ ፡ ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ልቀኝ ፡ እንጂ
ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ
ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x)
አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ
ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ
በጨለዬ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፡ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x)
ትምክህቴ ፡ ኩራቴ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ፣
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ እውነተኛ ፡ ወዳጄ
ትምክህቴ ፡ ኩራቴ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ፣ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ እውነተኛ ፡ አባቴ።