Mesfin Gutu/Selam New/Yemot Awaj
ርዕስ ፡ የሞት ፡ አዋጅ ዘማሪ ፡ መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ አልበም ፡ ሰላም ፡ ነው አዝ የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሰራም ፡ በሕይወቴ ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ ነገሩን ፡ አባቴ የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሰራም ፡ በሕይወቴ ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ
የሚውጠውን ፡ ፈልጐ ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ (፪x) ዙሪያ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢያንዣብብ ፡ ሰላሜን ፡ ደርሶ ፡ ሊነሳ (፪x) መጣ ፡ ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ ነደደ ፡ የአምላኬ ፡ ቁጣ (፪x) በእሳት ፡ ቅጥሩ ፡ ቀጠረኝ ጠላት ፡ በበቀል ፡ ሳይወጣ (፪x)
ስልጣን ፡ የለውም ፡ በኔ ፡ ላይ አለቃ ፡ አይሆንም ፡ የበላይ እንዲያው ፡ አይደለም ፡ መጓደዴ በመስቀል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ መወለዴ (፬x)
አዝ የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሰራም ፡ በሕይወቴ ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ ነገሩን ፡ አባቴ የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሰራም ፡ በሕይወቴ ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ
የስንቱን ፡ ጀግና ፡ ቤት ፡ ደፍሮ ፡ መቅሰፍቱን ፡ ይዞ ፡ ሲገባ (፪x) አሳየኝ ፡ ገና ፡ ከሩቁ ፡ አጥፊውን ፡ ገዳዩን ፡ ሌባ (፪x) ሸንጐ ፡ ሰብስቦ ፡ ሲመክር ፡ ታሪኬን ፡ መና ፡ ሊያደርገው (፪x) ምልክት ፡ ሰጥቶ ፡ አስመለጠኝ እኔ ፡ የማመልከው ፡ እንዲህ ፡ ነው (፪x)
ስልጣን ፡ የለውም ፡ በኔ ፡ ላይ አለቃ ፡ አይሆንም ፡ የበላይ እንዲያው ፡ አይደለም ፡ መጓደዴ በመስቀል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ መወለዴ (፬x)
አዝ የሞት ፡ አዋጅ ፡ አይሰራም ፡ በሕይወቴ (አይሰራም ፡ በሕይወቴ) አይሆንም ፡ በሕይወቴ (አይሆንም ፡ በሕይወቴ) ገልብጦታል ፡ ነገሩን ፡ አባቴ (ኢየሱስ ፡ አባቴ) (፪x)