Meserete Kristos Choir/Endiet Denq Amlak New/Endiet Denq Amlak New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ርዕስ ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው አልበም ፡ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው

የደን ፡ ልማቱ ፡ የገደል ፡ ስርገቱ የወንዝ ፡ እርዝመቱ ፡ የቀላይ ፡ ውበቱ የቆንጆ ፡ ገጽታው ፡ የቦታው ፡ ከፍታው የባሕር ፡ ጥልቀቱ ፡ የሜዳ ፡ ስፋቱ እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

የሽቶ ፡ መዓዛው ፡ የሙዚቃ ፡ ቃናው የለምለም ፡ እርካታው ፡ የመዝናኛ ፡ ቦታው የመፋቅር ፡ ወዙ ፡ የትዳር ፡ ማገዙ የፍጥረት ፡ ድምቀቱ ፡ የሰማይ ፡ ርቀቱ እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

የአበቦች ፡ ፍካታ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ የቀለም ፡ መዋሃድ ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ መዋደድ የእምነት ፡ እርካታ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ የፅዮን ፡ ውበቱ ፡ የእውነት ፡ ጥራቱ እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)

ጐህ ፡ ሲቀድ ፡ ማለዳ ፡ ጨለማ ፡ ሲከዳ የፀሐዩ ፡ ሙቀት ፡ የከዋክብት ፡ ብዛት የደመናት ፡ ክምር ፡ ንጹህ ፡ ተስማሚ ፡ አየር ሁሉን ፡ በስርዓት ፡ መሪ ፡ ለፍጥረቱ እኛ ፡ የምናመልከው ፡ መሠረቱ

አዝ፦ እንዴት ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምናመልከው እንደምን ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ እኛ ፡ የምንሰግድለት የኃይል ፡ ሁሉ ፡ ጉልበት ፡ የፍጥረት ፡ መሠረት (፪x)