Meserete Kristos Choir/Delu Yegietachen New/Oh Girum Hayl New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ርዕስ ፡ ኦ ፡ ግሩም ፡ ኃይል ፡ ነው አልበም ፡ ድሉ ፡ የጌታችን ፡ ነው

ኦ ፡ ግሩም ፡ ሃይል ፡ ነው (2) ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ በክንድህ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ኦ ፡ ግሩም ፡ ሃይል ፡ ነው

አዝ ፀሐይ ፡ ከዋክብትን ፡ በህዋ ፡ አንሳፈሃል መሬትን ፡ በተክል ፡ በውበት ፡ ፈጥረሃል ነፋስን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዲሆን ፡ አዘሃል በውን ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ግሩም ፡ ሃይል ፡ ይዘሃል

አዝ ላበቦች ፡ መዓዛን ፡ ለእንስሳት ፡ ማደሪያን ለኮከብ ፡ ጠፈርን ፡ ለአራዊትን ፡ ጫካን ለዓሣ ፡ ባህርን ፡ መኖሪያ ፡ አድርገሃል በውን ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ግሩም ፡ ሃይል ፡ ለብሰሃል

አዝ ተራራ ፡ ሸንተረር ፡ ወንዝንም ፡ ሜዳንም ፈጥረሃል ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የሚሳንህ ፡ የለም ጥበብን ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሰጥተሃል በውን ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ግሩም ፡ ሃይል ፡ ይዘሃል