ሊዲያ ፡ አንተነህ (lidya anteneh)
Jump to navigation
Jump to search
አንተን እያመለኩ አንተን እያከበርኩ
ውዴ እያመለኩ ውዴ እየወደድኩ
ላንተ እየዘመርኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
አንተን እየወደድኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
በደስታ በሙሉ ልቤ
ሳልሸራርፍ ይኸው ቃላቴ
ባይገኝ ሚመጥንህም አመልክሀለሁ እየኖርኩ
ትላንትን በሕያውነትህ
ዛሬንም በዐዲስነትህ
ነገንም በዘላለም ቤትህ
ላምልክህ ኾኜ በፊትህ...
ኑሮዬ ይኹን መሥዋዕትህ
ሕይወቴም ይኸው በፊትህ
በፍቅር፣ በእምነት በተስፋ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
ትላንትን በሕያውነትህ
ዛሬንም በዐዲስነትህ
ነገንም በዘላለም ቤትህ
ላምልክህ ኾኜ በፊትህ....
አመልክሀለሁ እየኖርኩ...