Kefa Mideksa/Hulum Yesma/Hulum Yesma

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search


ዘማሪ ፡ ኬፋ ፡ ሚደቅሳ አልበም ፡ ሁሉም ፡ ይስማ

አዝ

አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ
አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ

ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x)


ምደረ ፡ በዳውን ፡ አቋርጫለሁ
እጄን ፡ ይዘኸኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወት ፡ ኖሪያለሁ
አልነደፈኝም ፡ እባቡ ፡ ጊንጡ
አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ (፪x)
አቤት ፡ አባቴ ፡ በአንተ ፡ ተረፍኩ ፡ ከስንቱ


ሲጨላልም ፡ የማይነጋ ፡ ሲመስል
የቅርብ ፡ የሩቅ ፡ ገለል ፡ ገለል ፡ ሲል
በውድቅቱ ፡ ሌሊቱ ፡ መጣህና
በሰልፍ ፡ ቀን ፡ ራሴን ፡ ሸፈንክና
አዘመርከኝ (፫x)
እንዳዳንኩህ ፡ እንዳገዝኩህ ፡ መስክር ፡ አልከኝ
አባት ፡ ሆንከኝ ፡ ክብር ፡ ሆንከኝ ፡ ተሸከምከኝ
በደግ ፡ እጅህ ፡ እቅፍ ፡ አርገህ ፡ አነሳኸኝ


በምህረትህ ፡ ብዛት ፡ ቤት ፡ አግብተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x)
ቤት ፡ አግብተኸኛል
በፊትህ ፡ ቃል ፡ ደስታ ፡ ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል ፡ አሃሃ (፪x)
ለእኔ ፡ ሰጥተኸኛል
ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ የማመሰግንህ ፡ ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x)
ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው ከዛ ፡ ከጨካኙ ፡ ነፍሴን ፡ ከሚፈልግ
ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው ፡ አሃሃ (፪x)
ከአውሬ ፡ አስጥለኸኝ ፡ ነው

አዝ


አንተ ፡ እንደ ፡ ረዳኸኝ
አንተ ፡ እንዳነሳኸኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይወቅልኝ
ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ያመስግንልኝ (፪x)