Kefa Mideksa/Hulu Beju New/Qedus Egziabhier
Jump to navigation
Jump to search
ዘማሪ ፡ ኬፋ ፡ ሚደቅሳ ሌላ ፡ ሥም ፡ ቁፋ ፡ ሚዴቅሳ ርዕስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አልበም ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው
ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የነበርከው አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ከለላ ፡ የሆንከው (፬x)
ሌላማ ፡ ምን ፡ እከፍልሃለሁ ምሥጋና ፡ በፊትህ ፡ እሰዋለሁ (፪x)
አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ በሕይወት ፡ እንድኖር ፡ ያደረከኝ ከዚያ ፡ ከጨለማ ፡ ከሞት ፡ የታደከኝ ስለ ፡ እኔ ፡ የቆሰልከው ፡ የደቀቀከው ፡ ጌታ በልቤ ፡ ይኖራል ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ከሞት ፡ መትረፌ ይገርመኛል ፡ በአንተ ፡ መታቀፌ ይገርመኛል ፡ ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይገርመኛል ፡ ሆንክልኝ ፡ መከታ (፫x)
በረሃብ ፡ ዘመን ፡ ጥጋብ ፡ ሲሆንልኝ ፡ ያዩ ዛሬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አንተን ፡ ያመልካሉ እኔም ፡ በመደነቅ ፡ በመገረም ፡ ሆኜ አመልክሃለሁኝ ፡ በመቅደስህ ፡ ቆሜ (፪x)
ይገርመኛል ፡ ከሞት ፡ መትረፌ ይገርመኛል ፡ በአንተ ፡ መታቀፌ ይገርመኛል ፡ ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ይገርመኛል ፡ ሆንክልኝ ፡ መከታ (፫x)