ማነው (Manew) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

፯
(7)

አልበም
(Eyulegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2021)
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

እስትንፋስ ፡ ያላቸው ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
 እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ይላሉ
 አንዳንዱ ፡ ፈልጎ ፡ አንዳንዱ ፡ በግድ
አያስደንቅ ፡ ወይ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ሲሰግድን

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x
እንዳንተ ፡ ማነው?4x

አህዛብ ፡ ደንግጡ ፡ ምድርን ፡ ተፍራው
ፈላጭ ፡ ቆራጩ እሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
ታፍሮና ፡ ተከብሮት ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው
 ከእግዚአብሔር ፡ በስተቀር ፡ የትኛው ፡ አምላክ ፡ ነው?

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x
እንዳንተ ፡ ማነው?4x

የእድሜ ፡ ባለ ፡ ጸጋ ፡ ሁሌ ፡ አንፀባራቂ
ለሰማይ ፡ ለምድሩ ፡ ለፍጥረቱ ፡ በቂ
ከዘላለም ፡ በፊት ፡ ከጥንት ፡ የነበረው
እግዚአብሔርን ፡ በዕድሜ ፡ የሚበልጠው ፡ ማነው

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x
እንዳንተ ፡ ማነው?4x

የነገስታትን ፡ ወገብ ፡ የሚፈታ ፡ የሚፈታ ፡ ያኔ ፡ ጌታ
ብቻውን ፡ ብዙ ፡ ገጥሞ ፡ የሚረዳ ፡ የኔ ፡ ጌታ
ቃላቶች ፡ ተጨምቀው ፡ አንድ ፡ ቃል ፡ ቢሆኑም
ያንተን ፡ ትልቅነት ፡ ሊገልፁት ፡ አይችሉም

ማነው ፡ የላቀ ፡ የደመቀ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ
ማነው ፡ ያወቀ ፡ የረቀቀ ፡ ሁሌ ፡ የተደነቀ
ማነው ፡ የጸና ፡ ያልወደቀ ፡ ሁሌ ፡ እንደደመቀ
በትረ ፡ መንግስቱን ፡ ያለቀቀ ፡ ዘመኑ ፡ ያላለቀ

እናገራለሁኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብዬ
 እመሰክራለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብዬ
በግምት ፡ አይደለም ፡ የምናገረው
ሁሉን ፡ ቻይነቱን ፡ ስለማውቀው ፡ ነው
በመላ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ የምናገረው
ሁሉን ፡ ቻይነቱን ፡ ስለማውቀው ፡ ነው

ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ማነው?4x
እንዳንተ ፡ ማነው?4x