From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ካንተ የተነሳ በሆነልኝ ነገር
ከማመስገን በቀር እኔ ምን ልናገር
አስበህ አቅደህ በሰጠህኝ በሙሉ
ጌታ ስምህ ይክበር አመሰግናለሁ
ከኔ የሆነ የለም አንድም አለፋሁም
እንዲያው ሰትጠኸኟል ይህን አረሳሁም
ስለዚ ጌታዬ ለእኔ ስላረከው
ተረድቻለሁ ስምህን ላክበረው
አድርገህልኛል ካይምሮዬ በላይ
ጌታዬ ተባረክ በምድርም በሰማይም/3/
አድርገህልኛልና
ለዘላለም አመሰግንሀለው /6/
እድሜዬን በሙሉ ብለፋና ብጥር
የማላገኘውን ሰማያዊ ሚስጥር
ለልቤ ተናግረህ ልቤንም ማረከው
ከዚህ ሁሉ በላይ የራስሕህአረከዉ
እኔም ተስማምቼ በፍቅርህ ተማረኩኝ
አምላኬ ጌታዬ ምርጫዬ አደረኩኝ
አንተ ከመረጥከኝ ወዴት እሄዳለሁ
ካንተ የበለጠ ምንስ አገኛለሁ
ይህንን ላረከው በልብህ ላሰብከኝ
ለአንተ ለአምላኬ ሁሌ እገዛለሁኘ /3/
አድርገህልኛል
ለዘላለም አመሰግንሀለው /6/
ነፍሴንም ባረካት ሥጋዬንም ፈወስከው
ባርኮትህን ሁሉ በቤት አፈሰስከው
ወዳንተ መጥቼ ምንም አልጎደለኝ
ነፍስና ሥጋዬን በሙሉ ባረክልኝ
አለሁኝ በቤትህ ገናም እኖራለሁ
ስለምታቆመኝ እታመንሃለሁ
ንጉሴ ከሆንህ ቤቴን የምትገዛ
ይሄ ነው መሻቴ የለኝም ከዚህ ሌላ
ጌታዬ እና አምላኬ በሕይወቴ ላክብርህ
ይሄ ነው ምኞቴ ዘምኔን ልሰጥህ /2/
ይሄ ነው ምኞቴ እድሚዬን ልሰጥህ
አድርገህልኛል
ለዘላለም አመሰግንሀለው /6/
posted by natan mersha😊🙌✌
edited by MH :) ፡
|