Endalkachew Hawaz/Mesganawen Alresawem/Kef Bel
ከጥንት ፡ እንደሰማሁት
በዓይኖቼም ፡ ደግሞ ፡ እንዳየሁት
አምላክ ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ የለም
መቼም ፡ ቢሆን ፡ አይገኝም
በምድር ፡ ሆነ ፡ በሠማይ
በየብስ ፡ ሆነ ፡ በባሕር ፡ ላይ
በሰው ፡ ልጆችም ፡ መካከል
የለም ፡ አንተን ፡ የሚስተካከል
አዝ
ከፍ ፡ በል ፡ ለዘለዓለም ፡ ከፍ ፡ በል (፬x)
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ንጉሤ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ጌታዬ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ የማመልከው ፡ የለም
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ የማመልከው ፡ የለም (፪x)
ሰዎች ፡ የሚያመልኳቸው
ዛሬም ፡ የሚከተሏቸው
ብዙ ፡ አማልክት ፡ ቢኖሩም
አንዳቸውም ፡ እውነት ፡ አይደሉም
ታላቅ ፡ ገናና ፡ ኃይለኛ (ገናና ፡ ኃይለኛ)
ታጋሽ ፡ መሃሪ ፡ የሆንህ
ከጥንት ፡ ከጥንትም ፡ ጀምሮ (ጀምሮ)
በእውነት ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነህ
አዝ
ከፍ ፡ በል ፡ ለዘለዓለም ፡ ከፍ ፡ በል (፬x)
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ንጉሤ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ጌታዬ ነህ ፡ አንተ ፡ ለዘለዓለም
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ የማመልከው ፡ የለም
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ የማመልከው ፡ የለም (፪x)
በእኔ ፡ ላይ ፡ ተሹመሃል
ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ወርሶታል
እውነት ፡ በርታልኛለች
ነፍሴም ፡ አምላኳን ፡ አውቃለች
ውዴ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ
እኔም ፡ የአንተ ፡ ሆኛለሁ
በቀረልኝ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ
ሳደንቅህ ፡ ሳከብርህ ፡ ኖራለሁ
አዝ
ከፍ ፡ በል ፡ ለዘለዓለም ፡ ከፍ ፡ በል (፰x)