ቅዱስ (Kidus) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

፬
(4)

ህያው ምንጭ
(Heyaw Mench)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 6:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

እወድስሃለው በዜማ እወድስሃለው በቅኔ
የምስጋናዬ የአምልኮዬ መአዛው ይክበብህ
እንዲህ ነህ ብዬ በቃሌ አልገልጥህ አምላኬ ልዩ ነህ

አንተን ለማምለክ በመታደሌ
የደስታ እንባ ካይኖቼ ይፈሳል
አጥንት ጅማቴ ቅዱስ እያሉ
ልሳኔ ለአንተ ያቀነቅናል

እንደዘመርኩኝ እንደተቀኘሁ
እስከሰጠኽኝ እድሜ እኖራለው
ከእኔ እስኪወሰድ ይህ እስትንፋሴ
ሳቀርብ እኖራለው ለስምህ ቅኔ ውዳሴ

ኦ ምንኛ መታደል ነው (2x)
እግዚአብሔር አምላክ ለሆንከው ሰው (2X)
ኢየሱሴ ጌታ ለሆንከው ሰው (2X)

ለስምህ ክብር እዘምራለሁ
ታላቅ ነህ ልልህ አፌን እከፍታለሁ
እስከምመጣ መንግስተ ሰማይ
እጅ አጣምሬ ቁጭ ብዬ አላይ

እዚሁ ማምለክ እጀምራለሁ
ልኡል ሆይ አንተ ቅዱስ እላለሁ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ

ለቅድስና ምታሰቢያ ምስጋናን ፊትህ አቀርባለው
ብኪሩቤል ላይ ለተቀመጥከው የሚገባህን ክብር አበዛለው
ምስጋናና ዉበት በፊትህ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደስህ
ሞልተዉልሃል ተትረፍርፈው እኔም ምስጋናን ጨምራለው

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ