Elias Gemechu/Saychelem/Saychelem
1.ልቤ ፡ ያዘነው ፡ በራሱ ፡ ነገር
አልሰማ ፡ ብሎ ፡ ጌታው ፡ ሲናገር
ይሄ ፡ ጎዳና ፡ አይጠቅምም ፡ አለው
ልቤ ፡ ደንድኖ ፡ አልሰማም ፡ አለው፥
ልቤ ፡ ተጎዳ ፡ በራሴ
አልሰማ ፡ ብዬው ፡ ኢየሱሴን
ሸክምህ ፡ ይቅለልልህ ፡ ሲለኝ
አልፈልግ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ ሸሸሁኝ
አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እረ ፡ አልመሸም ፡ ገና
እረ ፡ አልመሸም ፡ ገና
አሁንም ፡ ጊዜ ፡ አለ ፡ ተመለስ ፡ እንደገና
አልረፈደም ገና
አልረፈደም ገና
አሁንም ፡ ጊዜ ፡ አለ ፡ ተመለስ ፡ እንደገና
2.ንጉሡ ፡ ሳኦል ፡ ጌታው ፡ ሲያዘው
አንድም ፡ እንዳይቀር ፡ አጥፋልኝ ፡ ሲለው
ለራሱ ፡ ምኞት ፡ ተሸነፈና
ይዞአቸው ፡ መጣ ፡ ማጥፋት ፡ ተወና
ቢደርስህ ፡ የ ፡ ንግሥ ፡ እጣ
አንተ ፡ ግን ፡ ከሀሳቡ ፡ ወጣህ
ከ ፡ ሳኦል ፡ አትማርም ፡ ወይ
የተጳፈው ፡ ላንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ ?
አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እረ ፡ አልመሸም ፡ ገና
3.ሙሽራውን ፡ ሊቀበሉ ፡ ወተው
ዘይት ፡ ትርፍ ፡ ይዘው ፡ ብርሀን ፡ ለኩሠው
ሲጠባበቁ ፡ ይመጣል ፡ እያሉ
በተስፋ ፡ ቆመው ፡ ፍፁም ፡ ሳይደክሙ
ሰነፍቹ ፡ ተዘናግተዋል
ዘይቱም ፡ ነዶ ፡ አልቆባቸዋል
ሙሽራው ፡ መቶ ፡ በሩን ፡ ዘጋው
በ ፡ እውንት ፡ አላውቃችሁም ።
አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እረ ፡ አልመሸም ፡ ገና፣
4.ሳይጨላልም ፡ ቶሎ ፡ ተመለስ
ምህረት ፡ ለምነህ ፡ በጊዜ ፡ ድረስ
ኃላ ፡ ካለፈ ፡ መመለሻህ
ሞት ፡ እንዳይመጣ ፡ እንዳይቀድምህ
ቀጠሮ ፡ አትስጠው ፡ ቶሎ ፡ ና
አምላክህ ፡ ይጠራሀል ፡ እና
የ ፡ አለም ፡ ዝናዋ ፡ ይቅርብህ
የ ፡ ዘላለም ፡ ህይወት ፡ ይብለጥብህ
አዝማች ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እረ ፡ አልመሸም ፡ ገና፣