ዶ/ር መላኩ ግርማ (Dr Melaku Girma)
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ፈቃድህ ፡ ይከናወናል
ሁሉን ፡ ልታደርግ ፡ ትችላለህ ፡ ሃሳብህን ፡ ማን ፡ ይከለክላል
በዓመታት ፡ መካከል ፡ ስራህን ፡ ሁሉ ፡ ሰርተሃል
አንተ ፡ ለዘላለም ፡ ጌታ ነህ በክብር ፡ ዙፋንህ ፡ ጸንተሃል
1/ሃይሌ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ከኔ ፡ በላይ ፡ ማነው ብሎ ፡ የታበየውን ፡ ወደ ፡ ታች ፡ ስትጥለው በቅን ፡ ስትፈርድ ፡ ስትገልጽ ፡ አንተነትህን ከቶ ፡ ምን ፡ አግዶህ ፡ ስታደርግ ፡ ፈቃድህን
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ፈቃድህ ፡ ይከናወናል ሁሉን ፡ ልታደርግ ፡ ትችላለህ ፡ ሃሳብህን ፡ ማን ፡ ይከለክላል በዓመታት ፡ መካከል ፡ ስራህን ፡ ሁሉ ፡ ሰርተሃል አንተ ፡ ለዘላለም ፡ ጌታ ነህ በክብር ፡ ዙፋንህ ፡ ጸንተሃል
2/ሃይልህን ፡ ያላወቁ ፡ ክንድህን ፡ ያልቀመሱ ክብርህን ፡ ሊጋፉ ፡ በእብሪት ፡ የተነሱ መታሰቢያህን ፡ ከምድር ፡ ሊያስወግዱ ፡ የለፉ በቁጣህ ፡ እስትንፋስ ፡ አለፉ ፡ እየጠፉ
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ፈቃድህ ፡ ይከናወናል ሁሉን ፡ ልታደርግ ፡ ትችላለህ ፡ ሃሳብህን ፡ ማን ፡ ይከለክላል በዓመታት ፡ መካከል ፡ ስራህን ፡ ሁሉ ፡ ሰርተሃል አንተ ፡ ለዘላለም ፡ ጌታ ነህ በክብር ፡ ዙፋንህ ፡ ጸንተሃል
3/ያምላክነትህን ፡ የዘለዓለም ፡ ሃይል
ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ በሁሉ ፡ ተገልጧል
ሥራህ ፡ ምስክር ፡ ነው ፡ ሰወች ፡ ቢያስተውሉ
ጌታ ፡ መሆንህ ፡ በፍጥረት ፡ በሙሉ
በሰማይና ፡ በምድር ፡ ፈቃድህ ፡ ይከናወናል ሁሉን ፡ ልታደርግ ፡ ትችላለህ ፡ ሃሳብህን ፡ ማን ፡ ይከለክላል በዓመታት ፡ መካከል ፡ ስራህን ፡ ሁሉ ፡ ሰርተሃል አንተ ፡ ለዘላለም ፡ ጌታ ነህ በክብር ፡ ዙፋንህ ፡ ጸንተሃል
4/አንተ ፡ የከፈትከውን ፡ ማነው ፡ የሚዘጋ
የዘጋኽውንስ ፡ ማን ፡ ከቶ ፡ ይከፍታል
ፈቃድህ ፡ በሙላት ፡ ሁልጊዜ ፡ ይሆናል
እንደሃሳብህ ፡ ላሉት ፡ ለበጎ ፡ ይፈጸማል