ርዕስ (Title) -

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

የደረጀ ፡ ከበደ ፡ መዝሙር
ካሴት 1
ምስጋና ፡ እልልታ
ጌታዬ ፡ አነባ ፡ ለኔ ፡ አለቀሰ
ሙትን ፡ ሊያድን ፡ ብሎ ፡ ደሙን ፡ አፈሰሰ
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ አለ ፡ ጮሀ ፡ ወዳባቱ
ሐሩር ፡ ቢወርድበት ፡ ቢበዛ ፡ ጭንቀቱ
              ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሃያሉ ፡ ጌታ
              ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሞተልን ፡ ጌታ

ከሰይጣን ፡ ተዋጋ ፡ በራብ ፡ ተፈተነ
እንዳልሆነ ፡ ሆነ ፡ በስደት ፡ ባከነ
ከግብፅ ፡ ቤተልሄም ፡ ከናዝሬት ፡ ይሁዳ
ጭንቅ ፡ ፍዳዉን ፡ አየ ፡ ለኔ ፡ ሲል ፡ ተጎዳ
                ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሞተልን ፡ ጌታ
                 ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሃያሉ ፡ ጌታ

ሄሮድስ ፡ ለሰይፍ ፡ አጨው ፡ ጲላጦስ ፡ ለሚስማር
መቼ ፡ ከቶ ፡ ደላው ፡ ሲኖር ፡ በዚች ፡ ምድር
በምኩራብ ፡ ተፈበት ፡ መስቀል ፡ አሳዘሉት
ቀራንዎ ፡ ሰቅለው ፡ ጎልጎታ ፡ ቀበሩት
               ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሞተልን ፡ ጌታ
               ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሃያሉ ፡ ጌታ

በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ፍዳ ፡ የኖረውን ፡ ጌታ
ነፍሴ ፡ ታመስግነው ፡ በመዝሙር ፡ በዕልልታ
ምስጋና ፡ ከሆነ ፡ የዉለታህ ፡ ካሳ
መዝሙሬን ፡ ተቀበል ፡ ዉዳሴ ፡ ሙገሳ

             ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሞተልን ፡ ጌታ
             ምስጋና ፡ እልልታ ፡ ይገባዋል ፡ ለርሱ ፡ ለሃያሉ ፡ ጌታ

[[Category:]]