From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
ጌታ ይታመናል
አይሆንም አልልም በእግዚአብሔር ይሆናል
አትችልም አልልም ለእርሱ ምን ይሳናል
የአራት ቀኑ እሬሳ ኮራ ብሎ መቷል
መርከብ ተሰባብሮ በሰላም ደርሰናል
ለደረቁ አጥንቶች ስጋ ለሌላቸው
ሂድ ተናገር አለኝ ሊያንቀሳቅሳቸው
በል ሲል የምልለት የእግዚአብሔር አፉ ነኝ
በደረቅ ነፈር ላይ ትንቢት አናገረኝ
አናገረኝ አናገረኝ
ይፈፅመዋል ምን ይሳነዋል/2
አይሆንም አልልም በእግዚአብሔር ይሆናል
አትችልም አልልም ለእርሱ ምን ይሳናል
የአራት ቀኑ እሬሳ ኮራ ብሎ መቷል
መርከብ ተሰባብሮ በሰላም ደርሰናል
መምህሩን አታድክም ልጅቷ ሞታለች
ብለው ተናገሩ ያማኝ አላማኞች
እመን እንጂ አትፍራ ተኝታለች አለው
ሞት እንቅልፍ ይሆናል ጌታን ለታመነው
ለታመነው ለታመነው
ሞት እንቅልፍ ይሆናል ጌታን ለታመነው
ሞት እንቅልፍ ይሆናል እርሱን ለታመነው
አይሆንም አልልም በእግዚአብሔር ይሆናል
አትችልም አልልም ለእርሱ ምን ይሳናል
የአራት ቀኑ እሬሳ ኮራ ብሎ መቷል
መርከብ ተሰባብሮ በሰላም ደርሰናል
አንካሶች ሲዘሉ እውሮች በርተዋል
ድንግሏም ወልዳለች ትንቢት ተደፅሟል
እኔም መልክት አለኝ ጌታ ይናገራል
ጌታ በታምራት ህዝቡን ያሻግራል
ያሻግራል ያሻግራል
ጌታ በታምራት ህዝቡን ያሻግራል/2
አይሆንም አልልም በእግዚአብሔር ይሆናል
አትችልም አልልም ለእርሱ ምን ይሳናል
የአራት ቀኑ እሬሳ ኮራ ብሎ መቷል
መርከብ ተሰባብሮ በሰላም ደርሰናል
እግዚአብሔር/4
ልዩ ነህ ክበር ክበር/4
|