በማዕበል ውስጥ ሆኖ (Bemaebel Wust Hono) - ዳዊት ፡ ጌታቸው

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)

፩
(1)

እጠብቅሀለሁ
(Etebikihalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

፫ (3)

ርዝመት (Len.): 4:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

በማዕበል ውስጥ ሆኖ ከአንተ ጋራ መሄድ ነው መሄድ ነው
በወጀብም መሃል ከአንተ ጋራ መሄድ ነው መሄድ ነው
በባሕር ላይ ሆኖ ከአንተ ጋራ በሚያስተጋባው
ተሽመድምዶ መቅረት ለምንድነው ግራ እንደገባው
ከቶ ለምን ይሆን ከአንተ ጋራ የምንፈራው
የዘወትር ልመና አሃሃሃ የምናደርሰው
 
ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው
በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x)
አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን
እንፈራለን ወጀቡን እያየን
እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን
ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን
 
(ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን
ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን) 2x
 
ለአእዋፍ ሁሉ አሃ የምታጠግብ ነህ
ለእኛ ለልጆችህ አሃ እንዴት ትነሳለህ
ብታደርግ ሁልጊዜ አሃ መች እናውቅሃለን
ስለሚቀጥለው ደግሞ ብዙ እናስባለን
ጌታ አንተን ብናይ አሃ ይህ ባልሆነ በእኛ
እምነት ጨምርልን ጌታ ሆይ አናውቅህምና

ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው
በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x)
አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን
እንፈራለን ወጀቡን እያየን
እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን
ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን
 
(ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን
ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን) 2x