Daniel Amdemichael/Yehonal/Ejeg Yakoragnal
ዘማሪ ፡ ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
ርዕስ ፡ እጅግ ፡ ያኮራኛል
አልበም ፡ ይሆናል
አዝ
እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኼው ፡ ነው።
ፍቅርህ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ በልጦብኛል
እንዳመልክህ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ ግድ ፡ ይለኛል
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴን ፡ ልናገረው
ተመስገን ፡ ከማለት ፡ ሌላ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴኑ ፡ ልናገረው
ምሥጋናዬ ፡ ምስጋና ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
እንዴት ፡ ብዬ ፡ የሆዴኑ ፡ ልናገረው
ምሥጋናዬ ፡ ምሥጋና ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው
አዝ
እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኼው ፡ ነው
ዛሬማ ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል ፡ ድንቅ ፡ ፍቅርህ
ሞገስ ፡ ሆኖኛል ፡ ጌታ ፡ ክቡር ፡ ሥምህ
በውዳሴ ፡ የተሞላ ፡ በምሥጋና
መዝሙር ፡ ይዘመርልህ ፡ የአንተ ፡ ነውና
በፈቃዴ ፡ ውዳሴን ፡ እጨምራለሁ
መድሃኒቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አነግስሃለሁ (፪x)
አዝ
እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት ፡ እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝን ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኼው ፡ ነው
ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነ ፡ ያማረለት
ከአምላኩ ፡ ጋር ፡ መንገዱ ፡ የቀናለት
ኤረ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ
ክቡር ፡ ሥምህን ፡ ልባርከው ፡ በዜማዬ
ክቡር ፡ ሥምህን ፡ አምላኬ ፡ ዛሬም ፡ ልባርከው
መድሃኒቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ አነግስሃለሁ (፪)
አዝ
እጅግ ፡ ያኮራኛል ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ
አተረፍኩኝ ፡ እንጂ ፡ አልከሰርኩም ፡ እኔ
አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ እቅድ ፡ ነው
ወደ ፡ ፍቅርህ ፡ መንግሥት እንድፈልስ ፡ ያደረገው
ክብርህን ፡ ላውራው ፡ ልናገረው
በሰጠኸኝ ፡ ዜማ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ የሆነልኝ ፡ ላሰማ ፡ ምሥጋና
ኩራት ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ሳስበው
ለአንተ ፡ መለየቴ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይኸው ፡ ነው