Daniel Amdemichael/Mognenet Hono Aydelem/Mognenet Hono Aydelem

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

ርዕስ ፡ ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም

አዝ

ሞኝነት ፡ ሆኖ ፡ አይደለም ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ነው

ና ፡ ሲለኝ ፡ የተከተልኩት ፡ ነፍሴ ፡ ተማርካ ፡ ነው

ጠቢባን ፡ ያላዩት ፡ ዕውቀት ፡ ለእኔ ፡ ተገልጦ ፡ ነው

የጌታን ፡ የማዳን ፡ ሚስጢር ፡ ነፍሴ ፡ ተረድታው ፡ ነው


ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ በልጦብኝ ፡ ነው

ከማንም ፡ በላይ ፡ ተመችቶኝ ፡ ነው

የቱ ፡ ነው ፡ ታዲያ ፡ ሞኝነቱ

ለእኔ ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ ጌታን ፡ ማወቁ ፡ ኤሄሄ (፪x)

አምላኬን ፡ ማወቄ አምላኬን ፡ ማወቄ ፡ አሃሃ/ኦሆሆ አምላኬን ፡ ማወቄ (፪x)


እኔስ ፡ መድኃኒቴን ፡ ተስፋ ፡ አደርገዋለሁ

እኔስ ፡ ኢየሱሴን ፡ ተስፋ ፡ አደርገዋለሁ

ቢጐድልም ፡ ቢሞላው ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ

እርሱ ፡ አይለየኝም ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ

ድንቁን ፡ አይቻለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ

ከኢየሱሴ ፡ በቀር ፡ ጌታ ፡ አላውቅም ፡ እኔ

ሞት ፡ ያላሸነፈው ፡ አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ

ዘመን ፡ የማይሽረው ፡ ነው ፡ የሌለው ፡ አቻ


አዝ

ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል

ከኃጢአት ፡ እሥራት ፡ ከደዌም ፡ ይፈታል

ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ እረፍትን ፡ ይሰጣል

ተስፋ ፡ ለቆረጡት ፡ ተስፋቸውን ፡ ያድሳል

ኃያላን ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ቢነሱ

ወድቀው ፡ ተረሱ ፡ እንጂ ፡ ለአፍታም ፡ አልታወሱ


የእኛ ፡ ግን ፡ ኢየሱስ ፡ በልባችን ፡ ያለው

ፍቅሩ ፡ የማይጠገብ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው


አዝ


ዓይኔ ፡ በርቶልኛል ፡ ጌታን ፡ አውቄያለሁ

ከዚህ ፡ በላይ ፡ የለም ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ

የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ በነጻ ፡ አግኝቻለሁ

በእርሱ ፡ ተመርጬ ፡ በፊቱ ፡ አዜማለሁ

እዘምራለሁኝ ፡ አልታክትም ፡ ሁሌ

ስለ ፡ እርሱ ፡ ዝም ፡ ልል ፡ ከቶ ፡ አልችልም ፡ እኔ

የማዳኑን ፡ ወንጌል ፡ በዜማ ፡ አወራለሁ

ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እመሰክራለሁ

አዝ