Daniel Amdemichael/Anbesa/Eyesus New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዳንኤል አምደሚካኤል
ርዕስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
አልበም ፡ አንበሳ

ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያከበረኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኝ
ዝም ፡ አልልም ፡ ለክብሩ ፡ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ ፡ አከብረዋለሁ (፪x)

ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ኤፍታህ ፡ ያለኝ ፡ ነኝ
ከሞት ፡ መልሶ ፡ ሕይወት ፡ የሰጠኝ
ዕዳዬ ፡ ተደምስሷል ፡ ነፃነቴም ፡ ታውጇል
ክብር ፡ ለሥሙ ፡ ይሁን ፡ ልቤ ፡ በኢየሱስ ፡ ረክቷል

አዝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያከበረኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኝ
ዝም ፡ አልልም ፡ ለክብሩ ፡ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ ፡ አከብረዋለሁ (፪x)

አንገት ፡ ያስደፋኝ ፡ ተሰበረ
ቅዱስ ፡ ጌታዬ ፡ በኔ ፡ ከበረ
ዛሬ ፡ ተፈትቻለው ፡ በምሥጋና ፡ ዘላለው
ሞገስ ፡ የሆነልኝን ፡ ኃያል ፡ ሥሙን ፡ ልባርከው (፪x)

አዝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያከበረኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኝ
ዝም ፡ አልልም ፡ ለክብሩ ፡ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ ፡ አከብረዋለሁ (፪x)

ሰላሙ ፡ እንደወንዝ ፡ ውስጤ ፡ ፈሰሰ
በረሃው ፡ ህይወቴም ፡ እረሰረሰ
ኢየሱሴ ፡ ወዶኛል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጎኛል
በሞገሱ ፡ ሸልሞ ፡ ለክብሩ ፡ አቁሞኛል (፪x)

አዝ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ያከበረኝ
ጌታዬ ፡ ነው ፡ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኝ
ዝም ፡ አልልም ፡ ለክብሩ ፡ ዘምራለሁ
ያከበረኝን /የባረከኝን/ ጌታ ፡ አከብረዋለሁ (፪x)

ጠላቴ ፡ ሰይጣን ፡ ወዴት ፡ አለህ
ሽክምህ ፡ ከላዬ ፡ ተንከባለለ
ከእጅህ ፡ ወጥቻለው ፡ የየሱሴ ፡ ሆኛለው
ለዘላለሙ ፡ ንጉስ ፡ ለሱ ፡ ተገዝቻለው (፪x)